Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 21:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዚያ ሕፃን ጋር ነበረ፤ አደ​ገም፤ በም​ድረ በዳም ተቀ​መጠ፤ ቀስ​ተ​ኛም ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እግዚአብሔር ከልጁ ጋራ ነበር፤ ልጁም እያደገ ሄደ፤ መኖሪያውንም በምድረ በዳ ውስጥ አደረገ፤ ጐበዝ ቀስተኛም ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እግዚአብሔርም ከብላቴናው ጋር ነበረ፥ አደገም፥ በምድረ በዳም ተቀመጠ፥ ቀስተኛም ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ልጁ እያደገ በሚሄድበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር፤ በፋራንም በረሓ ኖረ፤ ቀስት በመወርወርም የታወቀ አዳኝ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እግዚአብሔርም ከብላቴናው ጋር ነበረ፤ አደገም በምድረ በዳም ተቀመጠ፥ ቀስተኛም ሆነ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 21:20
13 Referencias Cruzadas  

እነ​ሆም፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር እሄ​ዳ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም መን​ገድ ሁሉ እጠ​ብ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ያ​ችም ምድር እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ሁሉ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ አል​ተ​ው​ህ​ምና።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አበ​ዛ​ለት፤ በግ​ዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገ​ስን ሰጠው።


እር​ሱም የበ​ረሃ ሰው ይሆ​ናል፤ እጁ በሁሉ ላይ ይሆ​ናል፤ የሁ​ሉም እጅ ደግሞ በእ​ርሱ ላይ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም በወ​ን​ድ​ሞቹ ሁሉ ፊት ይኖ​ራል።”


ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ጸና፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እስ​ከ​ታ​የ​በት ቀን ድረስ በም​ድረ በዳ ኖረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ለእ​ርሱ ተገ​ልጦ፥ “አንተ ጽኑዕ ኀያል ሰው! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው” አለው።


ብላ​ቴ​ኖ​ቹም አደጉ፤ ጐለ​መ​ሱም፤ ዔሳ​ውም አደን የሚ​ያ​ውቅ የበ​ረሃ ሰው ሆነ፤ ያዕ​ቆብ ግን ጭምት ሰው ነበረ፤ በቤ​ትም ይቀ​መጥ ነበር።


ስለ ይስ​ማ​ኤ​ልም እነሆ፥ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ እጅ​ግም አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለ​ቆ​ች​ንም ይወ​ል​ዳል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀያል አዳኝ ነበረ፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀያል አዳኝ እንደ ናም​ሩድ ተባለ።


አሁ​ንም ማደ​ኛ​ህን የፍ​ላ​ጻ​ህን አፎ​ትና ቀስ​ት​ህን ውሰድ፤ ወደ ምድረ በዳም ውጣ፤ አደ​ንም አድ​ን​ልኝ፤


ሕፃ​ኑም አደገ፤ በመ​ን​ፈ​ስም ጠነ​ከረ፤ ጥበ​ብ​ንም የተ​መላ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸጋ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios