Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አብ​ር​ሃ​ምም አለ፥ “ምን​አ​ል​ባት በዚህ ስፍራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ስለ​ሌለ በሚ​ስቴ ምክ​ን​ያት ይገ​ድ​ሉ​ኛል ብዬ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አብርሃምም አቢሜሌክን እንዲህ አለው፤ “ ‘እዚህ ቦታ ፈሪሀ እግዚአብሔር አለመኖሩን ተገነዘብሁ፤ ሰዎቹም ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል’ ብዬ ሠጋሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አብርሃምም አለ፦ “በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንደሌለ፥ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አብርሃምም አለ፤ በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንድሌለ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 20:11
16 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርን የሚፈልግ ዕውቀትን ከጽድቅ ጋር ያገኛል፥


የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ አምላክን ማወቅንም ታገኛለህ።


ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።


የዚህ ስፍራ ሰዎች ለር​ብቃ ሲሉ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ እር​ስ​ዋም ውብ ነበ​ረ​ችና።


የግ​ብፅ ሰዎች ያዩሽ እንደ ሆነ ሚስቱ ናት ይላሉ፤ እኔ​ንም ይገ​ድ​ሉ​ኛል፤ አን​ቺ​ንም በሕ​ይ​ወት ይተ​ዉ​ሻል።


ሰው​ንም፦ ‘እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራ​ቅም ማስ​ተ​ዋል ነው’ ” አለው።


በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ዮሴፍ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለ​ሁና።


እር​ሱም፥ “በብ​ላ​ቴ​ናው ላይ እጅ​ህን አት​ዘ​ርጋ፤ አን​ዳ​ችም አታ​ድ​ር​ግ​በት፤ ለም​ት​ው​ድ​ደው ልጅህ ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ለ​ት​ምና አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ እን​ደ​ሆ​ንህ አሁን ዐው​ቄ​አ​ለሁ” አለው።


በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት የለም።”


እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ ጥልንና ትዕቢትን፥ ክፉ መንገድንም ይጠላል። የክፉ ሰዎችንም ጠማማ መንገድ ጠላሁ።


የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


ኀጢ​አ​ተኛ በፊቱ የተ​ናቀ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈ​ሩ​ትን የሚ​ያ​ከ​ብር፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ምሎ የማ​ይ​ከዳ።


አው​ስ​ጢድ በሚ​ባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ይህን ነገር ማድ​ረ​ግህ ምን አይ​ተህ ነው?”


እር​ስ​ዋም ደግሞ በእ​ናቴ ወገን አይ​ደ​ለ​ችም እንጂ በእ​ው​ነት በአ​ባቴ ወገን እኅቴ ናት፤ ለእ​ኔም ሚስት ሆነች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios