Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በአ​ን​ደ​ኛው ቀን ከባ​ቢ​ሎን ሊወጡ ጀመሩ፤ መል​ካ​ሚ​ቱም የአ​ም​ላኩ እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 መልካሚቱ የእግዚአብሔር እጅ በርሱ ላይ ስለ ነበረች፣ ከባቢሎን በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ተነሥቶ በዐምስተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ኢየሩሳሌም ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በመጀመሪያው ወር በአንደኛው ቀን ከባቢሎን መውጣት ጀመረ፥ መልካሚቱም የአምላኩ እጅ በእርሱ ላይ ስለ ነበረች በአምስተኛ ወር በመጀመሪያው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የእግዚአብሔር ታላቅ ኀይል በእርሱ ላይ ስለ ነበረ ከባቢሎን በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ተነሥቶ ኢየሩሳሌም በአምስተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዕዝራ በመጀመሪያውም ወር በአንደኛው ቀን ከባቢሎን ሊወጣ ጀመረ፤ መልካሚቱም የአምላኩ እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና በአምስተኛ ወር በመጀመሪያው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 7:9
11 Referencias Cruzadas  

በን​ጉሡ ፊት በሚ​መ​ክ​ሩ​ትም፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም፥ በን​ጉሡ አለ​ቆች ሁሉ ፊት በእኔ ላይ ምሕ​ረ​ቱን ላከ። እኔም በእኔ ላይ ባለ​ችው በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በረ​ታሁ፤ ከእ​ኔም ጋራ ይወጡ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ቹን ሰበ​ሰ​ብሁ።


ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን ወጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠ​ውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአ​ም​ላ​ኩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና ንጉሡ ያሻ​ውን ሁሉ ሰጠው።


በን​ጉ​ሡም በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ።


በላ​ያ​ች​ንም መል​ካም በሆ​ነው በአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞ​ሐሊ ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውን አስ​ተ​ዋይ ሰው ሰራ​ብ​ያን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥራ ስም​ን​ቱን ልጆ​ቹ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አመ​ጡ​ልን።


ንጉ​ሡ​ንም፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ በሚ​ሹት ሁሉ ላይ ለመ​ል​ካም ነው፤ ኀይ​ሉና ቍጣው ግን እር​ሱን በሚ​ተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተና​ግ​ረን ነበ​ርና፤ በመ​ን​ገድ ካለው ጠላት ያድ​ኑን ዘንድ ጭፍ​ራና ፈረ​ሰ​ኞች ከን​ጉሡ እለ​ምን ዘንድ አፍሬ ነበ​ርና።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሄድ ዘንድ ከአ​ኅዋ ወንዝ ተነ​ሣን፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም እጅ በላ​ያ​ችን ነበረ፤ በመ​ን​ገ​ድም ከጠ​ላ​ትና ከሚ​ሸ​ምቅ ሰው እጅ አዳ​ነን።


ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ተቀ​መ​ጥን።


የአ​ም​ላ​ኬም እጅ በእኔ ላይ መል​ካም እንደ ሆነች፥ ንጉ​ሡም የነ​ገ​ረ​ኝን ቃል ነገ​ር​ኋ​ቸው። “ተነሡ እን​ሥራ” አል​ኋ​ቸው። እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለበጎ ሥራ አበ​ረቱ።


በቤ​ቱም አጠ​ገብ ላለው ለግ​ንብ በሮች፥ ለከ​ተ​ማ​ውም ቅጥር፥ ለም​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እን​ጨት እን​ዲ​ሰ​ጠኝ ለን​ጉሡ ዱር ጠባቂ ለአ​ሳፍ ደብ​ዳቤ ይሰ​ጠኝ” አል​ሁት። ንጉ​ሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከ​በ​ረች የአ​ም​ላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበ​ረ​ችና።


ታያ​ላ​ችሁ፤ ልባ​ች​ሁም ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች፤ አጥ​ን​ታ​ች​ሁም እንደ ለም​ለም ሣር ትበ​ቅ​ላ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ለሚ​ፈ​ሩት ትታ​ወ​ቃ​ለች፤ ዐላ​ው​ያ​ን​ንም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos