Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለሰ​ማይ አም​ላክ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን ወይ​ፈ​ኖ​ችና አውራ በጎች፥ ጠቦ​ቶ​ችም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እን​ዳሉ እንደ ካህ​ናቱ ቃል ስን​ዴና ጨው፥ የወ​ይን ጠጅና ዘይት የሚ​ጠ​ይ​ቋ​ች​ሁን ዕለት ዕለት ስጡ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ለሰማይ አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆን ዘንድ የሚያስፈልጋቸውን ነገር፣ ማለት ወይፈኖችን፣ አውራ በጎችንና ተባዕት ጠቦቶችን ስጧቸው፤ እንዲሁም ስንዴው፣ ጨዉ፣ የወይን ጠጁና ዘይቱ በኢየሩሳሌም ያሉት ካህናት በሚጠይቋችሁ መሠረት ያለ ማቋረጥ በየቀኑ ይሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ለሰማይ አምላክ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚያስፈልገውን፥ ወይፈኖችና አውራ በጎች ጠቦቶችም፥ በኢየሩሳሌም እንዳሉ እንደ ካህናቱ ቃል ስንዴና ጨው የወይን ጠጅና ዘይት ዕለት ዕለት ያለማቋረጥ ስጡአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህም ሁሉ ጋር በኢየሩሳሌም የሚገኙት ካህናት በሚነግሩአችሁ መሠረት በየዕለቱ በሰማይ ለሚኖረው አምላክ ለሚያቀርቡት መሥዋዕት የሚፈልጓቸውን ኰርማዎች፥ በጎችን ወይም ጠቦቶችን፥ እንዲሁም ለመባ የሚሆነውን ስንዴ፥ ጨው፥ የወይን ጠጅና የወይራ ዘይት ሁሉ ስጡአቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ለሰማይ አምላክ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚያስፈልገውን፥ ወይፈኖች፥ አውራ በጎችና ጠቦቶች፥ በኢየሩሳሌም እንዳሉ እንደ ካህናቱ ቃል ስንዴና ጨው የወይን ጠጅና ዘይት ዕለት ዕለት ያለማቋረጥ ስጡአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 6:9
13 Referencias Cruzadas  

ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶቹ በአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ዕቃ​ዎች በመ​ቅ​ደሱ ዕቃ ሁሉ፥ በመ​ል​ካ​ሙም ዱቄት፥ በወ​ይን ጠጁም፥ በዘ​ይ​ቱም፥ በዕ​ጣ​ኑም፥ በሽ​ቱ​ውም ላይ ሹሞች ነበሩ።


ይኸ​ውም ለሰ​ማይ አም​ላክ በጎ መዓዛ የሆ​ነ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ፥ ለን​ጉ​ሡና ለል​ጆ​ቹም ዕድሜ ይጸ​ልዩ ዘንድ ነው።


ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠሩ ዘንድ ለአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን፥ በወ​ንዝ ማዶ ካለው ሀገር ከሚ​መ​ጣው ግብር ከን​ጉሡ ገን​ዘብ ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች ወጭ​ውን በት​ጋት እን​ድ​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸው፥ ሥራም እን​ዳ​ታ​ስ​ፈ​ቱ​አ​ቸው አዝ​ዣ​ለሁ።


ነገ​ሥ​ታ​ትም አሳ​ዳ​ጊ​ዎች አባ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ እቴ​ጌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሞግ​ዚ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ግን​ባ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ አድ​ር​ገው ይሰ​ግ​ዱ​ል​ሻል፤ የእ​ግ​ር​ሽ​ንም ትቢያ ይል​ሳሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ እኔ​ንም በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ አያ​ፍ​ሩም።”


“ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መባ ከበ​ጎች ወይም ከፍ​የ​ሎች ቢሆን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን፥ የፊት እግ​ሮ​ቹ​ንና ራሱን ጨምሮ ያቀ​ር​በ​ዋል።


ሙሴም አሮ​ንን አለው፥ “ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋው እን​ቦ​ሳ​ውን፥ ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት አው​ራ​ውን በግ ወስ​ደህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​ባ​ቸው።


ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፤ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos