ዕዝራ 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ንጉሡንም ሲያቃልሉት ማየት አይገባንምና ስለዚህ ልከን ለንጉሡ አስታውቀናል፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 አሁንም እኛ ስለ ቤተ መንግሥቱ ስለሚገደን፣ የንጉሡም ክብር ሲነካ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው፣ ይህ ነገር በንጉሡ ዘንድ የታወቀ እንዲሆን ይህን መልእክት ልከናል፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ስለዚህ አሁን ሁላችን የቤተ መንግሥቱን ጨው እንበላለንና፥ የንጉሡ አለመከበር ማየት አይገባንምና ስለዚህ ልከን ለንጉሡ አስታወቅን፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እኛም የቤተ መንግሥቱ ጥቅም ተካፋዮች በመሆናችን አለመከበርዎን እያየን ዝም ማለትን ስላልወደድን ይህን ሐሳብ እናቀርባለን፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 የንጉሡንም ጨው እንበላለንና፥ ንጉሡንም ሲያቃልሉት ማየት አይገባንምና ስለዚህ ልከን ለንጉሡ አስታውቀናል፤ Ver Capítulo |