Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዕዝ​ራም ተነሣ፤ አለ​ቆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም፥ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ እን​ደ​ዚህ ቃል ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ማሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዕዝራም ተነሥቶ አለቆቹ ካህናት፣ ሌዋውያንና እስራኤል ሁሉ የቀረበውን ሐሳብ እንዲፈጽሙ አስማላቸው፤ እነርሱም ማሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹን፥ ካህናቱን፥ ሌዋውያኑንና እስራኤልንም ሁሉ እንደዚህ ቃል እንዲያደርጉ አስማላቸው፥ እነርሱም ማሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህም ዕዝራ የካህናት፥ የሌዋውያንና የቀሩት ሕዝብ መሪዎች ሸካንያ ባቀረበው ሐሳብ መስማማታቸውን በመሐላ እንዲያረጋግጡለት በማድረግ ሥራውን ጀመረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹንና ካህናቱን፥ ሌዋውያኑንና እስራኤልን ሁሉ እንደዚህ ቃል ያደርጉ ዘንድ አማለ፤ እነርሱም ማሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 10:5
10 Referencias Cruzadas  

እነ​ር​ሱ​ንም ተቈ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ረገ​ም​ኋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዐያ​ሌ​ዎ​ቹን መታሁ፤ ጠጕ​ራ​ቸ​ው​ንም ነጨሁ፤ እን​ዲ​ህም ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ል​ኋ​ቸው፥ “ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ።


እነ​ር​ሱም፥ “እን​መ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም አን​ሻም፤ እን​ደ​ተ​ና​ገ​ርህ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉ። ካህ​ና​ቱ​ንም ጠርቼ እን​ደ​ዚህ ነገር ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ል​ኋ​ቸው።


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።


ክፉ ሰው ግን ምክርን አይሰማትም፤ ለማኅበሩም መልካምና መጥፎ ነው የሚለው የለም።


ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጻድቅንም አስተምረው፥ ዕውቀትንም ያበዛል።


ጠቢብ እነዚህን በመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተ​ሰ​ጠው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ፥ ፍር​ዱ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ርግ​ማ​ን​ንና መሐ​ላን አደ​ረጉ።


አሁ​ንም እንደ ጌታ​ዬና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ትእ​ዛዝ እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ምክር፥ ሴቶ​ችን ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን እን​ሰ​ድድ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ጋር ቃል ኪዳን እና​ድ​ርግ። ተነሥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ትእ​ዛዝ ገሥ​ፃ​ቸው፤ እንደ ሕጉም ያድ​ርጉ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios