Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 42:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በዕቃ ቤቶ​ቹም ፊት በስ​ተ​ው​ስጥ ወርዱ ዐሥር ክንድ፥ ርዝ​መቱ መቶ ክንድ የሆነ መን​ገድ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከቱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ወርዱ ዐሥር ክንድ፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ የሆነ መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበር። የክፍሎቹም በሮች በሰሜን በኩል ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከክፍሎቹም ፊት ለፊት በውስጥ በኩል ወርዱ ዐሥር ክንድ ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ መንገድ ነበረ፤ መግቢያዎቹም በሰሜን በኩል ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከክፍሎቹ ፊት ለፊት በውስጥ በኩል ዐሥር ክንድ ወርድና መቶ ክንድ ርዝመት ያለው መተላለፊያ ነበር፤ መግቢያዎቹም በስተ ሰሜን በኩል ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በዕቃ ቤቶቹም ፊት በስተ ውስጥ ወርዱ አሥር ክንድ ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ መንገድ ነበረ፥ መዝጊያዎቻቸውም ወደ ሰሜን ይመለከቱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 42:4
5 Referencias Cruzadas  

በው​ጭም አደ​ባ​ባይ በሰ​ሜኑ መን​ገድ በም​ሥ​ራቅ በኩል አወ​ጣኝ፤ በል​ዩ​ውም ስፍራ አን​ጻ​ርና በሰ​ሜን በኩል በአ​ለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳ​ሉት አም​ስት ዕቃ ቤቶች አገ​ባኝ።


በስ​ተ​ፊ​ታ​ቸ​ውም የነ​በረ መን​ገድ በሰ​ሜን በኩል እንደ ነበ​ረው እንደ ዕቃ ቤቶቹ መን​ገድ አም​ሳል ነበር። ርዝ​መ​ታ​ቸ​ውም፥ ወር​ዳ​ቸ​ውም፥ መው​ጫ​ቸ​ውም፥ ሥር​ዐ​ታ​ቸ​ውም፥ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በዚ​ያው ልክ ነበሩ።


በበ​ሩም አጠ​ገብ በአ​ለው መግ​ቢያ ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ለካ​ህ​ናት ወደ​ሚ​ሆን ወደ ተቀ​ደ​ሰው ዕቃ ቤት አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በኋ​ላው በባ​ሕር በኩል አንድ ስፍራ ነበረ።


ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።


“ወደ ጠባቡ በር ትገቡ ዘንድ በርቱ፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሊገቡ የሚሹ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ግን አይ​ች​ሉም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos