Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ነ​ዚ​ያም እን​ስሳ ክን​ፎች እርስ በር​ሳ​ቸው ሲማቱ፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ችን ድምፅ፥ የታ​ላ​ቁ​ንም ንው​ጽ​ው​ጽታ ድምፅ ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ይህም የሕያዋኑ ፍጡራን ክንፎች እርስ በርስ ሲጋጩና በአጠገባቸው ያሉት መንኰራኵሮች የሚያሰሙት ታላቅ ህምህምታ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ይህም የሕያዋኑ ክንፎች እርስ በእርሳቸው ሲማቱ የሚወጣው ድምፅ፥ በአጠገባቸውም የነበሩት የመንኰራኵሮች ድምፅ ነበር፥ እርሱም ታላቅ የሚያጉረመርም ድምፅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የሕያዋን ፍጥረቶቹ ክንፎቹ እርስ በርሳቸው በአየር ላይ ሲፋጩ ሰማሁ፤ ከመንኰራኲሮቹም የሚሰማው የጋጋታ ድምፅ ከፍተኛ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የአራቱም እንስሳ ክንፎች እርስ በርሳቸው ሲማቱ፥ በአጠገባቸውም የመንኰራኵሮችን ድምፅ፥ የጽኑውንም ንውጥውጥታ ድምፅ ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 3:13
6 Referencias Cruzadas  

በሾ​ላ​ውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽ​ው​ሽ​ውታ ድምፅ ስት​ሰማ፥ በዚያ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ለመ​ም​ታት በፊ​ትህ ወጥቶ ይሆ​ና​ልና በዚያ ጊዜ ፍጠን” አለው።


በየ​መ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም ሁሉ አራት የናስ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም የሚ​ዞ​ሩ​በ​ትን የናስ ወስ​ከ​ምት ሠራ፤ ከመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውም ሰን በታች በአ​ራቱ ማዕ​ዘን በኩል አራት በም​ስል የፈ​ሰሱ እግ​ሮች ነበሩ።


ስመ​ለ​ከ​ትም፥ እነሆ በአ​ራቱ እን​ስ​ሶች አጠ​ገብ በም​ድር ላይ አንድ መን​ኰ​ራ​ኵር አየሁ።


ሲሄ​ዱም የክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅ ሠራ​ዊ​ትም ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆ​ሙም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስቡ ነበር።


የኪ​ሩ​ቤ​ልም የክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ድምፅ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላክ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ረው ያለ ድምፅ እስከ ውጭው አደ​ባ​ባይ ድረስ በሩቅ ይሰማ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos