Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 26:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በባ​ሕር ውስጥ የመ​ረብ ማስጫ ትሆ​ና​ለች፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ብዝ​በዛ ትሆ​ና​ለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እኔ ጌታ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፤ በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆናለች፤ አሕዛብም ይበዘብዟታል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ትሆናለች፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ፤ ለሕዝቦችም ብዝበዛ ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እዚያው በባሕር መካከል አጥማጆች መረባቸውን ለማድረቅ የሚያሰጡበት ስፍራ አደርጋታለሁ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ ሕዝቦች ጢሮስን ይመዘብራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ትሆናለች፥ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ለአሕዛብም ብዝበዛ ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 26:5
6 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ እነሆ እጄን ዘር​ግ​ቼ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አስ​በ​ዘ​ብ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም ለይች እቈ​ር​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ከሀ​ገ​ሮ​ችም እደ​መ​ስ​ስ​ሃ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ሃ​ለ​ሁም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”


እንደ ተራ​ቈተ ድን​ጋይ አደ​ር​ግ​ሻ​ለሁ፤ የመ​ረ​ብም ማስጫ ትሆ​ኛ​ለሽ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ሠ​ሪም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰው እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ባድማ ከተማ ባደ​ረ​ግ​ሁሽ ጊዜ፥ ቀላ​ዩ​ንም ባወ​ጣ​ሁ​ብሽ ጊዜ፥ ብዙ ውኆ​ችም በከ​ደ​ኑሽ ጊዜ፥


ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ሙሾን ያሞ​ሹ​ል​ሻል፤ በባ​ሕር መካ​ከል እንደ ታወ​ከች እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነበር? ይላሉ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የግ​ብ​ፅን ምድር ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳል፤ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ብዝ​በ​ዛ​ዋ​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛል፤ ይህም ለሠ​ራ​ዊቱ ደመ​ወዝ ይሆ​ናል።


ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችም ከዓ​ይ​ን​ጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይ​ን​ኤ​ግ​ላ​ይም ድረስ በዚያ ይቆ​ማሉ። ያም መረብ መዘ​ር​ጊያ ይሆ​ናል፤ ዓሣ​ዎ​ችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ​ዎች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እጅግ ይበ​ዛሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos