Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 23:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በግ​ብፅ ሀገር አመ​ነ​ዘሩ፤ በኮ​ረ​ዳ​ነ​ታ​ቸው ሳሉ አመ​ነ​ዘሩ፤ በዚ​ያም ጡቶ​ቻ​ቸው ወደቁ፤ በዚ​ያም ድን​ግ​ል​ና​ቸ​ውን አጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ገና በወጣትነታቸው ዘማውያት በመሆን በግብጽ ሳሉ አመነዘሩ፤ በዚያችም ምድር አጐጠጐጤአቸው ተዳበሰ፤ የድንግልናቸውም ጕያ በእጅ ተሻሸ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በግብጽ አመነዘሩ፤ በወጣትነታቸው አመነዘሩ፤ በዚያ ጡቶቻቸው ተዳሰሱ፥ በዚያም የድንግልናቸው የጡቶች ጫፍ ተዳበሱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነርሱም በወጣትነታቸው ወራት በግብጽ ሲኖሩ ክብርናቸውን አጥተው በመዋረድ አመንዝሮች ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በግብጽም አመነዘሩ፥ በኰረዳነታቸው አመነዘሩ፥ በዚያ ጡቶቻቸው ምዋሸሹ በዚያም የድንግልናቸውን ጡቶች ዳበሱ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 23:3
17 Referencias Cruzadas  

ዝሙ​ቷም ከንቱ ሆነ፤ እር​ስ​ዋም ከድ​ን​ጋ​ይና ከግ​ንድ ጋር አመ​ነ​ዘ​ረች።


“ነገር ግን በው​በ​ትሽ ታም​ነ​ሻል፤ በስ​ም​ሽም አመ​ን​ዝ​ረ​ሻል፤ ምን​ዝ​ር​ና​ሽ​ንም ከመ​ን​ገድ አላፊ ሁሉ ጋር አበ​ዛሽ።


ከኀ​ጢ​አ​ት​ሽና ከዝ​ሙ​ትሽ ሁሉ ይህ ይከ​ፋል፤ አንቺ ዕራ​ቁ​ት​ሽን ሳለሽ፥ ኀፍ​ረ​ትም ሞል​ቶ​ብሽ ሳለሽ፥ በደ​ም​ሽም ተለ​ው​ሰሽ ሳለሽ፥ የሕ​ፃ​ን​ነ​ት​ሽን ወራት አላ​ሰ​ብ​ሽም።


እኔም፦ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ ያስ​ወ​ግድ፤ በግ​ብ​ፅም ጣዖ​ታት አት​ር​ከሱ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ አል​ኋ​ቸው።


እነ​ርሱ ግን ዐመ​ፁ​ብኝ፤ ይሰ​ሙ​ኝም ዘንድ አል​ወ​ደ​ዱም፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ርኵ​ሰ​ቱን ከፊቱ አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ የግ​ብ​ጽ​ንም ጣዖ​ታት አል​ተ​ወም፤ በዚ​ህም ጊዜ በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል ቍጣ​ዬን እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸው ዘንድ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ነገር ግን በግ​ብፅ ምድር ያመ​ነ​ዘ​ረ​ሽ​በ​ትን የወ​ጣ​ት​ነ​ት​ሽን ዘመን አስ​በሽ ዝሙ​ት​ሽን አበ​ዛሽ።


ጡትሽ በአ​ጐ​ጠ​ጐጠ ጊዜ በማ​ደ​ሪ​ያሽ በግ​ብፅ ሀገር የሠ​ራ​ሽ​ውን የወ​ጣ​ት​ነ​ት​ሽን ኀጢ​አት አሰ​ብሽ።”


ትጠ​ጪ​ዋ​ለሽ፥ ትጨ​ል​ጪ​ው​ማ​ለሽ፤ በዓ​ላ​ት​ሽ​ንና መባ​ቻ​ዎ​ች​ሽን እሽ​ራ​ለሁ፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስማ​ቸ​ውም የታ​ላ​ቂቱ ሐላ የታ​ናሽ እኅ​ቷም ሐሊባ ነበረ፤ እኔም አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለዱ። ስማ​ቸ​ውም ሐላ ሰማ​ርያ ናት፤ ሐሊባ ደግሞ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ናት።


እኔም፦ ‘አሁን ከእ​ር​ስዋ ጋር ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ እር​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለች፤’ አልሁ።


በግ​ብ​ፅም የነ​በ​ረ​ውን ዝሙ​ቷን አል​ተ​ወ​ችም፤ በዚ​ያም በኮ​ረ​ዳ​ነቷ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኝ​ተው ነበር፤ የድ​ን​ግ​ል​ና​ዋ​ንም ጡቶች ዳብ​ሰው ነበር፤ ዝን​የ​ታ​ቸ​ው​ንም አፍ​ስ​ሰ​ው​ባት ነበር።


ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃሉ መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆሴ​ዕን፥ “ምድ​ሪቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቃ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለ​ችና ሂድ፤ ዘማ​ዊ​ቱን ሴትና የዘ​ማ​ዊ​ቱን ልጆች ለአ​ንተ ውሰድ” አለው።


ከዚ​ያም የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ብ​ዋን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ምክ​ር​ዋ​ንም በአ​ኮር ሸለቆ እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ እንደ ሕፃ​ን​ነ​ትዋ ወራት፥ ከግ​ብ​ፅም እንደ ወጣ​ች​በት ቀን ትዘ​ም​ራ​ለች።


መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሞ ተከ​ት​ለው ላመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ቸው ለሰ​ይ​ጣ​ናት አይ​ሠዉ። ይህ ለእ​ነ​ርሱ ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።”


ነገር ግን እኛ በግ​ብፅ ምድር እንደ ተቀ​መ​ጥን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ባለ​ፋ​ች​ሁ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ መካ​ከል እን​ዳ​ለ​ፍን ዐው​ቃ​ች​ኋ​ልና፥


“አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት፤ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነ​ትም አም​ል​ኩት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በወ​ንዝ ማዶ፥ በግ​ብ​ፅም ውስጥ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አም​ልኩ።


በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል፤ እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos