Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እጅ​ህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስ​ሳም በም​ድ​ርም ቡቃያ ሁሉ ላይ በረዶ ይሆ​ናል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “በመላዪቱ የግብጽ ምድር ባሉት ሰዎች፣ በእንስሳት እንዲሁም በምድሪቱ ላይ በሚበቅሉት ነገሮች ሁሉ ላይ በረዶ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ አንሣ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ በሰው፥ በከብት፥ በእርሻ ቡቃያ ሁሉ ላይ፥ በግብጽ ምድር ሁሉ በረዶ እንዲሆን እጅህን ወደ ሰማያት ዘርጋ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በረዶም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ይዘንባል፤ ሕዝቡን፥ እንስሶቹ በእርሻ ያለውን ተክል ሁሉ ይመታል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “በግብፅ አገር በሰው፥ በእንስሳም፥ በእርሻም ቡቃያ ሁሉ ላይ፥ በግብፅ አገር ሁሉ በረዶ ይሆን ዘንድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 9:22
7 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እጅ​ህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ላይ ጨለማ ይሁን፤ ጨለ​ማ​ውም የሚ​ዳ​ሰስ ነው” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ውሰድ፤ በግ​ብፅ ውኆች፥ በወ​ን​ዞ​ቻ​ቸው፥ በመ​ስ​ኖ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በኩ​ሬ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በውኃ ማከ​ማ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ላይ እጅ​ህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆ​ናል፤” በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በዕ​ን​ጨት ዕቃና በድ​ን​ጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን በእ​ጅህ ዘርጋ፤ የም​ድ​ሩ​ንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማ​ልም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ይወ​ጣል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ይዘህ በወ​ን​ዞ​ቹና በመ​ስ​ኖ​ዎቹ፥ በውኃ ማከ​ማ​ቻ​ዎ​ቹም ላይ እጅ​ህን ዘርጋ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ች​ንም አውጣ’ ” በለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በልቡ ያላ​ሰበ ግን ከብ​ቶ​ቹን በሜዳ ተወ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እየ​ሸሹ በቤ​ት​ሖ​ሮን ቍል​ቍ​ለት ሲወ​ርዱ፥ ወደ ዓዜ​ቃና ወደ መቄዳ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ታላ​ላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውና ሞቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ይፍ ከገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ይልቅ በበ​ረዶ ድን​ጋይ የሞ​ቱት በለጡ።


በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos