Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሙሴም ፈር​ዖ​ንን፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ ከአ​ንተ፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም እን​ዲ​ጠፉ፥ በወ​ን​ዙም ብቻ እን​ዲ​ቀሩ፥ ለአ​ንተ፥ ለሹ​ሞ​ች​ህም፥ ለሕ​ዝ​ብ​ህም መቼ እን​ድ​ጸ​ልይ ቅጠ​ረኝ” አለው። ፈር​ዖ​ንም፥ “ነገ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሙሴም ፈርዖንን፣ “በአባይ ወንዝ ካሉት በቀር ከአንተና ከቤቶችህ ጓጕንቸሮቹ እንዲወገዱ ለአንተ፣ ለሹማምትህና ለሕዝብህ የምንጸልይበትን ጊዜ እንድትወስን ለአንተ ትቼዋለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታም እንደ ሙሴ ቃል አደረገ፤ እንቁራሪቶቹም በየቤቶቹ፥ በየመንደሮቹና በሜዳም ሞቱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “በደስታ እጸልይልሃለሁ፤ ለአንተና ለመኳንንትህ ለሕዝብህም የምጸልይበትን ሰዓት ብቻ ወስንልኝ፤ ከዚያም በኋላ ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ ርቀው በዐባይ ወንዝ ብቻ ተወስነው እንዲኖሩ አደርጋለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሙሴም ፈርዖንን፥ “ጓጕንቸሮቹ ከአንተም ከቤቶችህም እንዲጠፋ፥ በወንዙም ብቻ እንዲቀሩ፥ ለአንተ ለባሪያዎችህም ለሕዝብህም መቼ እንድጸልይ አስታውቀኝ፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 8:9
8 Referencias Cruzadas  

“በውኑ መጥ​ረ​ቢያ በሚ​ቈ​ር​ጥ​በት ሰው ላይ ይነ​ሣ​ልን? ወይስ መጋዝ በሚ​ስ​በው ሰው ላይ ይጓ​ደ​ዳ​ልን? ይህም ዘንግ በሚ​መ​ቱ​በት ላይ እንደ መነ​ሣት፥ በት​ርም ዕን​ጨት አይ​ደ​ለ​ሁም እንደ ማለት ነው።”


ኤል​ያ​ስም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት፥ “እና​ንተ ብዙ​ዎች ናች​ሁና አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ አንድ ወይ​ፈን ምረ​ጡና አዘ​ጋጁ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም ስም ጥሩ፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አት​ጨ​ምሩ” አላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከአ​ንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝ​ቶ​አል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል፦ እጄ አዳ​ነኝ ብሎ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ይ​ብኝ እኔ ምድ​ያ​ምን በእ​ጃ​ቸው አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።”


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹን ከእኔ፥ ከሕ​ዝ​ቤም እን​ዲ​ያ​ርቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝ​ቡን እለ​ቅ​ቃ​ለሁ” አላ​ቸው።


ሙሴም፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ታውቅ ዘንድ እሺ እንደ አልህ ይሁን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወን​ዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈ​ጸመ።


ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከአ​ንተ፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም፥ ከመ​ን​ደ​ሮ​ች​ህም፥ ከሹ​ሞ​ች​ህም፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም ይሄ​ዳሉ፤ በወ​ን​ዙም ብቻ ይቀ​ራሉ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios