ዘፀአት 8:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ሙሴም፥ “እነሆ፥ ከአንተ ዘንድ እወጣለሁ፤ ወደ እግዚአብሔርም እጸልያለሁ፤ የውሻ ዝንቡም ከአንተ፥ ከሹሞችህና ከሕዝብህ ነገ ይርቃል፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ ሕዝቡን እንደማትለቅቅ እንደገና ማታለልን አትድገም።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ሙሴም እንዲህ አለ፤ “ከአንተ እንደ ተለየሁ ወዲያውኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነገም ዝንቡ ሁሉ ከፈርዖን፣ ከሹማምቱና ከሕዝቡ ይወገዳል። ብቻ ሕዝቡ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲሠዉ ባለመፍቀድ ከዚህ ቀደም ፈርዖን አታልሎ እንዳደረገው አሁንም እንዳያደርግ ርግጠኛ ይሁን።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በነገው ቀን ዝንቦቹ ከአንተና ከመኳንንቱ ከሕዝቡም ዘንድ እንዲወገዱ ከአንተ እንደ ተለየሁ አሁኑኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ እንዳይሄዱ በመከልከል እንደገና ልታሞኘኝ አይገባም።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ሙሴም፥ “እነሆ ከአንተ ዘንድ እወጣለሁ፤ የዝንቡም መንጎች ከፈርዖን፥ ከባሪያዎቹም፥ ከሕዝቡም ነገ እንዲሄዱ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እንዳይለቅቅ ፈርዖን እንደገና አያታልለን” አለ። Ver Capítulo |