Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ቀድሞ ያደ​ር​ጉት የነ​በ​ረ​ውን የጡብ ቍጥር እን​ዲሁ በየ​ቀኑ በእ​ነ​ርሱ ላይ አድ​ር​ጉት፤ ምንም ከእ​ርሱ አታ​ጕ​ድሉ፤ ሥራ ሰል​ች​ተ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ፦ ‘ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እን​ድ​ን​ሠዋ እን​ሂድ’ እያሉ ይጮ​ሃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሆኖም ቀድሞ በሚያቀርቡት ሸክላ ልክ ሠርተው እንዲያቀርቡ አድርጓቸው። የሥራ ድርሻቸውን አትቀንሱ። ሰነፎች ናቸው፤ ‘ሄደን ለአምላካችን መሥዋዕት እንሠዋ’ የሚሉትም ለዚህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን የጡብ ቍጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፦ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ መሄድ እንፈልጋለን’ እያሉ ይጮኸሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ነገር ግን ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን ያኽል አንድ ጡብ እንኳ ሳይጐድል እንዲያስረክቡ አድርጉ፤ ‘ለአምላካችን መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ልቀቀን!’ እያሉ የሚነዘንዙኝ ብዙ የሚሠሩት ነገር ስለሌለ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ቀድሞ ያደርጉት የነበረውን የጡብ ቁጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ምንም ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፥ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ እንሂድ’ እያሉ ይጮኻሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 5:8
6 Referencias Cruzadas  

ችግ​ረ​ኛ​ንም በች​ግሩ ረዳው፤ እንደ ሀገር በጎች አደ​ረ​ገው።


በብ​ርቱ ሥራም ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ዘንድ የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆ​ችን ሾመ​ባ​ቸው፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም ፌቶ​ምን፥ ራም​ሴ​ንና የፀ​ሐይ ከተማ የም​ት​ባል ዖንን ጽኑ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ።


እርሱ ግን፥ “እና​ንተ አር​ፋ​ች​ኋል፤ ቦዝ​ና​ች​ኋል፤ ስለ​ዚ​ህም፦ ‘እን​ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ሠዋ’ ትላ​ላ​ችሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አለ​ቆች ዕለት ዕለት ከም​ት​ሠ​ሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታ​ጕ​ድሉ ባሉ​አ​ቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋ​ባ​ቸው አዩ።


“እንደ ወት​ሮው ለጡብ ሥራ ደግሞ ገለባ ለሕ​ዝቡ አት​ስጡ፤ ነገር ግን እነ​ርሱ ሄደው ለራ​ሳ​ቸው ገለባ ይሰ​ብ​ስቡ።


በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ላይ ሥራው ይክ​በ​ድ​ባ​ቸው፤ ይህን ብቻ ያስ​ባሉ፤ ከንቱ ቃልም አያ​ስ​ቡም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos