Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ደግ​ሞም አለው፥ “እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ባያ​ም​ኑህ፥ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ምል​ክት ቃል​ህን ባይ​ሰሙ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪቱ ምል​ክት ቃል​ህን ያም​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔርም፣ “እንግዲህ ባያምኑህ ወይም የመጀመሪያውን ታምራዊ ምልክት ባይቀበሉ እንኳ ሁለተኛውን ያምናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “እንዲህ ይሆናል፤ ባያምኑህ የፊተኛይቱንም ምልክት ቃል ባይሰሙ፥ የኋላኛይቱን ምልክት ቃል ያምናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ በመጀመሪያው ተአምር ባያምኑና እውነት ነው ብለው ባይቀበሉህ፥ ሁለተኛውን ተአምር ያምናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ደግሞም አለው፦ “እንዲህም ይሆናል፤ ባያምኑህ የፊተኛይቱንም ምልክት ነገር ባይሰሙ፥ የሁለተኛይቱን ምልክት ነገር ያምናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 4:8
10 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ባነ​በበ ጊዜ ልብ​ሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለ​ምጹ እፈ​ውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስ​ደዱ እኔ በውኑ ለመ​ግ​ደ​ልና ለማ​ዳን የም​ችል አም​ላክ ነኝን? ተመ​ል​ከቱ፥ የጠብ ምክ​ን​ያት እን​ደ​ሚ​ፈ​ል​ግ​ብኝ ተመ​ል​ከቱ” አለ።


እርሱ ይሰ​ብ​ራል፥ ዳግ​መ​ኛም ይጠ​ግ​ናል፤ ይቀ​ሥ​ፋል፥ እጆ​ቹም ይፈ​ው​ሳሉ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከ​ውን ቃል ሁሉ፥ የአ​ዘ​ዘ​ው​ንም ተአ​ም​ራት ሁሉ ለአ​ሮን ነገ​ረው።


ዳግ​መ​ኛም፥ “እጅ​ህን ወደ ብብ​ትህ መልስ” አለው። እጁ​ንም ወደ ብብቱ መለ​ሳት፤ “እጅ​ህን ከብ​ብ​ትህ አውጣ” አለው፤ እጁ​ንም ከብ​ብቱ አወጣ፤ ተመ​ል​ሳም ገላ​ውን መሰ​ለች።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እነ​ዚ​ህን ሁለት ምል​ክ​ቶች ባያ​ምኑ፥ ቃል​ህ​ንም ባይ​ሰሙ፥ ከወ​ንዙ ውኃን ውሰድ፤ በደ​ረ​ቁም መሬት ላይ አፍ​ስ​ሰው፤ ከወ​ን​ዙም የወ​ሰ​ድ​ኸው ውኃ በደ​ረቁ መሬት ላይ ደም ይሆ​ናል።”


ሕማ​ምን በሕ​ማም ላይ፥ ተስ​ፋ​ንም በተ​ስፋ ላይ ተቀ​በሉ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው።


ይህ​ንም ያህል ተአ​ም​ራት በፊ​ታ​ቸው ሲያ​ደ​ርግ አላ​መ​ኑ​በ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤ እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


ጌዴ​ዎ​ንም፥ “በፊ​ትህ ሞገ​ስን ካገ​ኘሁ፥ የም​ት​ና​ገ​ረ​ኝም አንተ እንደ ሆንህ ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos