Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 39:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ በአ​ክ​ሊሉ ላይ ያን​ጠ​ለ​ጥ​ሉት ዘንድ ሰማ​ያ​ዊ​ውን ፈትል አሰ​ሩ​በት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ከመጠምጠሚያው ጋራ ለማያያዝ ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው በመጠምጠሚያው ላይ እንዲያንጠለጥሉት ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እርሱንም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከመጠምጠሚያው ፊት በሰማያዊ ክር አሰሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 በመጠምጠሚያውም ላይ ያንጠለጥሉት ዘንድ ሰማያዊውን ፈትል አሰሩበት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 39:31
5 Referencias Cruzadas  

የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ልብ​ሶች እነ​ዚህ ናቸው፤ ልብሰ እን​ግ​ድዓ፥ ልብሰ መት​ከፍ፥ ቀሚ​ስም፥ ዥን​ጕ​ር​ጕር እጀ ጠባብ፥ መጠ​ም​ጠ​ሚያ፥ መታ​ጠ​ቂ​ያም፤ እነ​ዚ​ህ​ንም በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን፥ ለል​ጆ​ቹም የተ​ቀ​ደሰ ልብስ ያድ​ርጉ።


“ከጥሩ ወር​ቅም የወ​ርቅ ቅጠል ሥራ፤ በእ​ር​ሱም እንደ ማኅ​ተም ቅርጽ አድ​ር​ገህ፦ ቅድ​ስና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚል ትቀ​ር​ጽ​በ​ታ​ለህ።


ከጥሩ ወርቅ የተ​ለየ የወ​ርቅ ቅጠል ሠሩ፤ በእ​ር​ሱም እንደ ማኅ​ተም ቅርጽ አድ​ር​ገው፥ “ቅድ​ስና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” የሚል ጻፉ​በት።


እን​ዲ​ሁም የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ማኅ​በ​ሩ​ንም ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሰበ​ሰበ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios