Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 37:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ የዘ​ረጉ ሆኑ፥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ሸፈኑ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተያዩ፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ መክ​ደ​ኛው ተመ​ለ​ከቱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ኪሩቤልም የስርየት ክዳኑን በመሸፈን ክንፋቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ነበር፤ ኪሩቤል ወደ ስርየት መክደኛው እየተመለከቱ እርስ በርሳቸው ገጽ ለገጽ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ የዘረጉ ነበሩ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ሸፈኑ፥ እርስ በርሳቸውም ትይዩ ነበሩ፥ የኪሩቤል ፊቶቻቸው ወደ መክደኛው ይመለከት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘርግተው መክደኛውን በመሸፈን እርስ በርስ እንዲተያዩ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ የዘረጉ ሆኑ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ሸፈኑ፥ እርስ በርሳቸውም ተያዩ፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ መክደኛው ተመለከቱ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 37:9
15 Referencias Cruzadas  

ሕል​ምም አለመ፤ እነ​ሆም መሰ​ላል በም​ድር ላይ ተተ​ክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ይወ​ጡ​በ​ትና ይወ​ር​ዱ​በት ነበር።


አዳ​ም​ንም አስ​ወ​ጣው፤ ደስታ በሚ​ገ​ኝ​ባት በገ​ነት አን​ጻ​ርም አኖ​ረው፤ ወደ ሕይ​ወት ዛፍ የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም መን​ገድ ለመ​ጠ​በቅ የም​ት​ገ​ለ​ባ​በጥ የነ​በ​ል​ባል ሰይ​ፍን በእ​ጃ​ቸው የያዙ ኪሩ​ቤ​ልን አዘ​ዛ​ቸው።


ሁለ​ቱም ኪሩ​ቤል በው​ስ​ጠ​ኛው ቤት መካ​ከል ነበሩ። የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ን​ዱም ኪሩብ ክንፍ አን​ደ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ ክንፍ ሁለ​ተ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ቱም ክን​ፎች በቤቱ መካ​ከል እርስ በር​ሳ​ቸው ይነ​ካኩ ነበር።


ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ ይዘ​ረ​ጋሉ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ይሸ​ፍ​ናሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እርስ በርሱ ይተ​ያ​ያል፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ ስር​የት መክ​ደ​ኛው ይሁን።


ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ፥ ቁመ​ቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆ​ነ​ውን ገበታ ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ።


ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ጋር አን​ዱን ኪሩብ በአ​ንድ ወገን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ በሌላ ወገን በዚ​ህና በዚያ ሁለ​ቱን ኪሩ​ቤል ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው በላይ ሠራ፤


ሱራ​ፌ​ልም በዙ​ሪ​ያው ቆመው ነበር፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ስድ​ስት ክንፍ ነበ​ረው፤ በሁ​ለቱ ክን​ፎ​ቻ​ቸው ፊታ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ይበ​ርሩ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “በበ​ለስ ዛፍ ሥር አየ​ሁህ ስለ አል​ሁህ አመ​ን​ህን? ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ታያ​ለህ” አለው።


እኛስ ሁላ​ችን ፊታ​ች​ንን ገል​ጠን በመ​ስ​ተ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እና​ያ​ለን፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ እንደ ተሰ​ጠን መጠን የእ​ር​ሱን አር​አያ እን​መ​ስል ዘንድ ከክ​ብር ወደ ክብር እን​ገ​ባ​ለን።


ብዙ ልዩ ልዩ የሆ​ነች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኩል በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለ​ቆ​ችና ሥል​ጣ​ናት ትታ​ወቅ ዘንድ፤


ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት።


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?


ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos