Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 37:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከጥሩ ወር​ቅም ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስ​ር​የት መክ​ደኛ ሠራ​ላት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ከንጹሕ ወርቅ የስርየት መክደኛ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከንጹሕ ወርቅ የስርየት መክደኛ ሠራ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ርዝመቱ መቶ ዐሥር ሳንቲ ሜትር ስፋቱም ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከጥሩ ወርቅም ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 37:6
11 Referencias Cruzadas  

በላ​ይ​ዋም ማስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ውን የሚ​ጋ​ርዱ የክ​ብር ኪሩ​ቤል ነበሩ፤ ነገር ግን በየ​መ​ልኩ እና​ገ​ረው ዘንድ ዛሬ ጊዜው አይ​ደ​ለም።


እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ነገር ግን ቀጠ​ሮው በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ።


እር​ሱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት የሚ​ገኝ፥ በደ​ሙም የሆነ ማስ​ተ​ስ​ረያ አድ​ርጎ አቆ​መው፤ ይህም ከጥ​ንት ጀምሮ በበ​ደ​ሉት ላይ ጽድ​ቁን ይገ​ልጥ ዘንድ ነው።


ዳዊ​ትም ለመ​ቅ​ደሱ ወለል፥ ለቤ​ቱም፥ ለቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም፥ ለደ​ር​ቡና ለው​ስ​ጡም ጓዳ​ዎች፥ ለስ​ር​የ​ቱም መክ​ደኛ መቀ​መጫ ምሳ​ሌ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን፥ የቃል ኪዳ​ኑ​ንም ታቦት፥ በእ​ር​ሱም ላይ ያለ​ውን የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውን፥ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ዕቃ ሁሉ፤


ታቦ​ቷ​ንም ለመ​ሸ​ከም በታ​ቦቷ አጠ​ገብ ባሉት አራት ቀለ​በ​ቶች መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋን አገባ።


ሁለት ኪሩ​ቤ​ል​ንም ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሠራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን አደ​ረ​ጋ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios