Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 36:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሙሴም ባስ​ል​ኤ​ል​ንና ኤል​ያ​ብን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕው​ቀ​ት​ንና ጥበ​ብን በል​ቡ​ና​ቸው ያሳ​ደ​ረ​ባ​ቸ​ው​ንና ጥበብ ያላ​ቸ​ውን፥ ሥራ​ው​ንም ለመ​ሥ​ራት ይቀ​ርብ ዘንድ ልቡ ያስ​ነ​ሣ​ውን ሁሉ ሥራ​ውን ሠር​ተው ይፈ​ጽሙ ዘንድ ጠራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም ሙሴ ባስልኤልንና ኤልያብን እንዲሁም እግዚአብሔር ችሎታ የሰጣቸውን፣ መጥተው ሥራውን ለመሥራት ፈቃደኛ የሆኑትን ጥበብ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ አስጠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሙሴም ባስልኤልን፥ ኤልያብንና ጌታ በልቡ ጥበብን ያሳደረበትን ጥበበኛ ሰው ሁሉ፥ ሥራውን ለመሥራት ልቡ ያነሣሣውን ሁሉ ጠራቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ሙሴም ባጽልኤልንና ኦሆሊአብን፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ልዩ ችሎታ የሰጣቸውንና ለመርዳት ፈቃደኞች የነበሩትን ሌሎችን ጥበበኞች ሁሉ ጠርቶ ሥራውን እንዲጀምሩ ነገራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሙሴም ባስልኤልንና ኤልያብን፥ እግዚአብሔርም በልቡ ጥበብን ያደረገለትን በልብ ጥበበኛ ሰው ሁሉ፥ ሥራውንም ለመሥራት ይቀርብ ዘንድ ልቡ ያስነሣውን ሁሉ ጠራቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 36:2
15 Referencias Cruzadas  

እነ​ሆም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ የሚ​ሆኑ የካ​ህ​ና​ትና የሌ​ዋ​ው​ያን ክፍ​ሎች በዚህ አሉ፤ ለሁ​ሉም ዓይ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ትና ሥራ በጥ​በ​ብና በነ​ፍሱ ፈቃድ የሚ​ሠራ ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አለ​ቆ​ችና ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈጽ​መው ይታ​ዘ​ዙ​ሃል” አለው።


በሠ​ራ​ተ​ኞች እጅ ለሚ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ለወ​ርቁ ዕቃ ወር​ቁን፥ ለብ​ሩም ዕቃ ብሩን ሰጥ​ቻ​ለሁ። ዛሬ በዚች ቀን በፈ​ቃዱ አገ​ል​ግ​ሎ​ቱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ፈ​ጽም ማን ነው?”


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በል​ባ​ችሁ ያሰ​ባ​ች​ሁ​ትን ከገ​ን​ዘ​ባ​ችሁ መባ አም​ጡ​ልኝ” በላ​ቸው።


በተ​ራራ ላይ እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ እን​ድ​ት​ሠራ ተጠ​ን​ቀቅ።


አን​ተም የጥ​በብ መን​ፈስ ለሞ​ላ​ሁ​ባ​ቸው፥ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ተና​ገር። እነ​ር​ሱም ካህን ሆኖ እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ለአ​ሮን ለቤተ መቅ​ደስ የሚ​ሆን የተ​ለየ ልብስ ይሥሩ፤


እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚ​ሆን የአ​ሂ​ሳ​ሚ​ክን ልጅ ኤል​ያ​ብን ሰጠሁ፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ዕው​ቅ​ትን ሰጠሁ።


“በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ፥ በልቡ ጥበ​በኛ የሆነ ሁሉ መጥቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ያድ​ርግ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ታር​ፋ​ለህ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ የሚ​ሠ​ራ​በ​ትም ሁሉ ይሙት።


“ባስ​ል​ኤ​ልና ኤል​ያብ፥ ለመ​ቅ​ደ​ስም ማገ​ል​ገያ ሥራ ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን የሰ​ጣ​ቸው በል​ባ​ቸ​ውም ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አደ​ረጉ።”


እነ​ር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለመ​ቅ​ደስ ማገ​ል​ገያ ሥራ ያመ​ጡ​ትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀ​በሉ። እነ​ዚ​ያም እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው ማለዳ ማለዳ ስጦ​ታ​ውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።


ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ቀሳ​ው​ስ​ትን ሾሙ፤ ጾሙ፤ ጸለ​ዩም፤ ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አደራ ሰጡ​አ​ቸው።


አክ​ር​ጳ​ንም “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾ​ም​ህ​ባ​ትን መል​እ​ክ​ት​ህን እን​ድ​ት​ፈ​ጽ​ማት ተጠ​ን​ቀቅ” በሉት።


እንደ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ጠራ በቀር፥ ማንም ለራሱ ክብ​ርን የሚ​ወ​ስድ የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos