Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 30:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከክ​ፈ​ፉም በታች ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አድ​ር​ግ​ለት። በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለቱ ጐን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱን ያነ​ሡ​ባ​ቸው ዘንድ የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎቹ መግ​ቢያ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች የሚይዙ፣ ከክፈፉ በታች ትይዩ የሆኑ ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ለመሠዊያው አብጅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከአክሊሉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አድርግለት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ በእነርሱ እንዲሸከሙም የመሎጊያዎቹ ማስገቢያ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህ መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች እንዲገቡበት ከክፈፉ ሥር አያይዛቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት። በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች ስፍራ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:4
8 Referencias Cruzadas  

አራት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶ​ችም አድ​ር​ግ​ለት፤ እነ​ር​ሱ​ንም በአ​ራቱ እግ​ሮቹ ላይ አኑር፤ በአ​ንድ ወገን ሁለት ቀለ​በ​ቶች፥ በሌላ ወገን ሁለት ቀለ​በ​ቶች ይሁኑ።


ለታ​ቦቱ መሸ​ከ​ሚያ በታ​ቦቱ ጎን ባሉት አራት ቀለ​በ​ቶች መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን አግባ።


ቀለ​በ​ቶ​ቹም ገበ​ታ​ውን ለመ​ሸ​ከም መሎ​ጊ​ያ​ዎቹ እን​ዲ​ሰ​ኩ​ባ​ቸው በክ​ፈፉ አቅ​ራ​ቢያ ይሁኑ።


ሳን​ቆ​ቹን በወ​ርቅ ለብ​ጣ​ቸው፤ ቀለ​በ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም የመ​ወ​ር​ወ​ሪያ ቤት እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው ከወ​ርቅ ሥራ​ቸው፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም በወ​ርቅ ለብ​ጣ​ቸው።


ለመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም እንደ መረብ ሆኖ የተ​ሠራ የናስ መከታ አድ​ር​ግ​ለት፤ ለመ​ከ​ታ​ውም አራት የናስ ቀለ​በት በአ​ራት ማዕ​ዘኑ አድ​ር​ግ​ለት።


መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ስት​ሸ​ከሙ መሎ​ጊ​ያ​ዎቹ በመ​ሠ​ዊ​ያው በሁ​ለት ወገን ይሁኑ።


ወለ​ሉ​ንና የግ​ድ​ግ​ዳ​ው​ንም ዙሪያ፥ ቀን​ዶ​ቹ​ንም በጥሩ ወርቅ ትለ​ብ​ጠ​ዋ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የጥሩ ወርቅ ክፈፍ ታደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለህ።


መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ በወ​ር​ቅም ለብ​ጣ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos