Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 30:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሮ​ንም በዓ​መት አንድ ጊዜ በቀ​ን​ዶቹ ላይ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ር​ጋል፤ በዓ​መት አንድ ጊዜ ኀጢ​አ​ትን ከሚ​ያ​ነ​ጻው ደም ይወ​ስ​ዳል፤ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ነጻ ያደ​ር​ጋል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አሮን በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርግበታል፤ ይህ ዓመታዊ ማስተስረያ በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ለማስተስረያ ከሚሆን የኀጢአት መሥዋዕት ደም ጋራ መደረግ አለበት፤ ይህም ለእግዚአብሔር እጅግ ቅዱስ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አሮን በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል፤ በዓመት አንድ ጊዜ ለትውልዳችሁ ማስተስረያ በሚሆን በኃጢአት መሥዋዕት ደም ማስተስረያ ያደርግበታል። ለጌታ እጅግ የተቀደሰ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ከታረደው እንስሳ ደም ወስዶ በአራቱም ጒጦች ላይ በማድረግ መሠዊያው የሚነጻበትን ሥርዓት ይፈጽም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዓመቱ ይፈጸም፤ በዚህ ዐይነት ይህ መሠዊያ ለእግዚአብሔር በፍጹም የተቀደሰ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሮንም በአመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል፤ በአመት አንድ ጊዜ ለልጅ ልጃችሁ ማስተስረያ በሚሆን በኃጢአት መሥዋዕት ደም ማስተስረያ ያደርግበታል። ለእግዚአብሔር ቅድስተ ቅዱሳን ናት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:10
18 Referencias Cruzadas  

በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወዳ​ለው ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጥቶ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም፥ ከፍ​የ​ሉም ደም ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ያሉ​ትን ቀን​ዶች ያስ​ነ​ካል።


ሊቀ ካህ​ናቱ ያደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ በያ​መ​ቱም ደም ይዞ ወደ ቅድ​ስት ይገባ እንደ ነበረ ዘወ​ትር ራሱን የሚ​ሠዋ አይ​ደ​ለም።


“በዚህ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን የማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን ናት፤ ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቋት፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ።


ወደ ሁለ​ተ​ኛ​ዪቱ ክፍል ግን ሊቀ ካህ​ናቱ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ደም ይዞ፥ በየ​ዓ​መቱ አንድ ጊዜ ብቻ​ውን ይገባ ነበር።


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


ስድስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ካለ በወርቅ ከተሠራ መሠዊያ ቀንዶች አንድ ድምፅ ሰማሁ፤


ሌላም ዕጣን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አታ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም፤ የመ​ጠ​ጥም ቍር​ባን አታ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስ​ር​የቱ መክ​ደኛ ላይ በደ​መ​ናው ውስጥ እታ​ያ​ለ​ሁና እን​ዳ​ይ​ሞት በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ወዳ​ለው ወደ ስር​የቱ መክ​ደኛ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ሁል​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ገባ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን ንገ​ረው።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርኩ​ስ​ነት፥ ከመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም፥ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ለመ​ቅ​ደሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ እን​ዲ​ሁም በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው መካ​ከል ከእ​ነ​ርሱ ጋር ለኖ​ረች ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ያደ​ር​ጋል።


አዶ​ን​ያ​ስም ከሰ​ሎ​ሞን ፊት የተ​ነሣ ፈራ፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀንድ ያዘ።


አሮ​ንና ልጆቹ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕ​ጣ​ኑም መሠ​ዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።


ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለው ጣፋጭ ዕጣን በሚ​ታ​ጠ​ን​በት መሠ​ዊያ ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ የወ​ይ​ፈ​ኑ​ንም ደም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባለው በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያው ቀን​ዶች ላይ ከደሙ ያደ​ር​ጋል፤ ደሙ​ንም ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ባለው ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በታች ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios