Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 27:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ለማ​ገ​ል​ገል ሁሉ የድ​ን​ኳን ዕቃ ሁሉ፥ አው​ታ​ሮቹ ካስ​ማ​ዎ​ቹም ሁሉ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ካስ​ማ​ዎች ሁሉ የናስ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጥቅማቸው ምንም ዐይነት ይሁን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ከንሓስ የተሠሩ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ለአገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፥ ካስማዎቹ ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ፥ የነሐስ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በድንኳኑ ውስጥ የሚገኙት ለማናቸውም ጥቅም የሚውሉ የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎች ሁሉ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ለማገልገል ሁሉ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፥ ካስማዎቹም ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ፥ የናስ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 27:19
14 Referencias Cruzadas  

ከእርሱ ዘንድ የማዕዘኑ ድንጋይ፥ ከእርሱም ዘንድ ችንካሩ፥ ከእርሱም ዘንድ የሰልፍ ቀስት፥ ከእርሱም ዘንድ አስገባሪው ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ።


እነሆ፥ የመ​ድ​ኀ​ኒ​ታ​ች​ንን ከተማ ጽዮ​ንን ተመ​ል​ከት፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ድን​ኳ​ኖ​ችዋ የማ​ይ​ና​ወጡ፥ ካስ​ማ​ዎ​ችዋ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የማ​ይ​ነ​ቀሉ፥ አው​ታ​ሮ​ች​ዋም ሁሉ የማ​ይ​በ​ጠሱ፥ የበ​ለ​ጸ​ገች ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ያያሉ።


የጠ​ቢ​ባን ቃል እንደ በሬ መው​ጊያ ነው፥ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​ትም ከአ​ንድ እረኛ የተ​ሰ​ጡት ቃላት እንደ ተቸ​ነ​ከሩ ችን​ካ​ሮች ናቸው።


አሁ​ንም ቅሬታ ይተ​ዉ​ልን ዘንድ፥ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ስፍ​ራው ኀይ​ልን ይሰ​ጠን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም ዐይ​ና​ች​ንን ያበራ ዘንድ፥ በባ​ር​ነ​ትም ሳለን ጥቂት የሕ​ይ​ወት መታ​ደ​ስን ይሰ​ጠን ዘንድ ለጥ​ቂት ጊዜ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥቂት ዕረ​ፍ​ትን አገ​ኘን።


በዙ​ሪ​ያ​ውም የሚ​ቆ​ሙት የአ​ደ​ባ​ባዩ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቹም፥ የአ​ደ​ባ​ባዩ ደጃፍ መጋ​ረጃ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹም፥ አው​ታ​ሮ​ቹም፥ ዕቃ​ዎ​ቹና ማገ​ል​ገ​ያ​ዎቹ ሸክ​ማ​ቸው ነው፤ የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ት​ንም የሸ​ክ​ማ​ቸ​ውን ዕቃ ሁሉ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጠሩ።


ዕቃ​ውም ሁሉ፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ውም ሁሉ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም የሚ​ቆሙ የአ​ደ​ባ​ባይ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቹም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹም፥ አው​ታ​ሮ​ቹም ይሆ​ናሉ።


የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም መጋ​ረ​ጆች፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹ​ንም፥ እግ​ሮ​ቹ​ንም፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ አው​ታ​ሮ​ቹ​ንም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹ​ንም፥ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማገ​ል​ገያ የሚ​ሆ​ኑ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ፤


በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ ያሉ​ትን እግ​ሮች፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ እግ​ሮች፥ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ካስ​ማ​ዎች ሁሉ፥ በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪ​ያም ያሉ​ትን ካስ​ማ​ዎች ሁሉ አደ​ረገ።


የድ​ን​ኳ​ኑም ካስ​ማ​ዎች፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያሉ የአ​ደ​ባ​ባዩ ካስ​ማ​ዎች የናስ ነበሩ።


የማ​ደ​ሪ​ያ​ውን ካስ​ማ​ዎች፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ካስ​ማ​ዎች፥ አው​ታ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም፤


ለመ​ሠ​ዊ​ያው ክዳን ሥራ​ለት፤ መሸ​ፈ​ኛ​ውን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ የሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹን፥ የእ​ሳት መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አድ​ርግ። ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አድ​ርግ።


የአ​ደ​ባ​ባዩ ርዝ​መት በየ​ገጹ መቶ ክንድ፥ ስፋ​ቱም በየ​ገጹ አምሳ ክንድ ይሁን፤ የመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ከፍታ አም​ስት ክንድ ይሁን፤ መጋ​ረ​ጃ​ውም ከጥሩ በፍታ፥ እግ​ሮ​ቹም ከናስ የተ​ሠሩ ይሁኑ።


“አን​ተም መብ​ራ​ቱን ሁል ጊዜ ያበ​ሩት ዘንድ ለመ​ብ​ራት ተወ​ቅጦ የተ​ጠ​ለለ ጥሩ የወ​ይራ ዘይት እን​ዲ​ያ​መ​ጡ​ልህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እዘ​ዛ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios