Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሙሴና አሮ​ንም እነ​ዚ​ህን ተአ​ም​ራ​ቶ​ችና ድን​ቆች ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ለመ​ል​ቀቅ እንቢ አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሙሴና አሮንም እነዚህን ድንቅ ታምራት በፈርዖን ፊት አደረጉ። ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ ፈርዖንም እስራኤላውያን ከአገሩ ለቅቀው እንዲሄዱ አልፈቀደም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራቶች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ፤ ጌታም የፈርዖንን ልብ አጸና፥ የእስራኤልንም ልጆች ከአገሩ አልለቀቀም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራት በንጉሡ ፊት አደረጉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ ስላደነደነ እስራኤላውያን ከምድሪቱ እንዲወጡ አልፈቀደላቸውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራቶች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ፤ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና፤ የእስራኤልንም ልጆች ከአገሩ አልለቀቀም።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 11:10
17 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ ሊለ​ቅ​ቃ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ደም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አል​ል​ቀ​ቀም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ሉን የሚ​ገ​ል​ጽ​በ​ትን ቅጣ​ቱን ሊያ​ሳይ ቢወድ፥ ትዕ​ግ​ሥ​ቱን ካሳየ በኋላ ለማ​ጥ​ፋት የተ​ዘ​ጋ​ጁ​ትን ቍጣ​ውን የሚ​ገ​ል​ጽ​ባ​ቸ​ውን መላ​እ​ክት ያመ​ጣል።


በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኀይ​ለ​ኛም፥ ታላ​ቅም ነው፤ ክፉስ ሆኖ በፊቱ የቆመ ማን ነው?


ግብ​ጻ​ው​ያ​ንና ፈር​ዖ​ንም ልባ​ቸ​ውን እን​ዳ​ጸኑ ልባ​ች​ሁን ለምን ታጸ​ና​ላ​ችሁ? በተ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸው ጊዜ ያወ​ጡ​አ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምን? እነ​ር​ሱም አል​ሄ​ዱ​ምን?


የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳ​ል​ፈን ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን አደ​ን​ድ​ኖ​ታ​ልና፥ ልቡ​ንም አጽ​ን​ቶ​ታ​ልና።


“በዐ​ይ​ና​ቸው አይ​ተው፥ በል​ባ​ቸ​ውም አስ​ተ​ው​ለው እን​ዳ​ይ​መ​ለ​ሱና እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ታወሩ፤ ልባ​ቸ​ውም ደነ​ደነ።”


እነሆ፥ የሚ​ወ​ድ​ደ​ውን ይም​ረ​ዋል፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ልቡን ያጸ​ና​ዋል።


እኔም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም ድን​ቄ​ንና ተአ​ም​ራ​ቴን አበ​ዛ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙ​ሴና ለአ​ሮን እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብፅ ሀገር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ይ​ራ​ሩ​ላ​ቸው ፈጽ​መው እን​ዲ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይጋ​ጠሙ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ደ​ነ​ድኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን አጸና።


አቤቱ፥ ከመ​ን​ገ​ድህ ለምን አሳ​ት​ኸን? እን​ዳ​ን​ፈ​ራ​ህም ልባ​ች​ንን ለምን አጸ​ና​ህ​ብን? ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ ርስ​ትህ ነገ​ዶች ተመ​ለስ፤


ነገር ግን በጽኑ እጅ ካል​ሆነ በቀር ትሄዱ ዘንድ የግ​ብፅ ንጉሥ እን​ደ​ማ​ይ​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ችሁ እኔ አው​ቃ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios