Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤፌሶን 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በሕ​ግም ተስፋ ያለው የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ትእ​ዛዝ ይህ ነው፥ “አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “አባትህንና እናትህን አክብር” በሚለው ቀዳሚ ትእዛዝ ውስጥ ያለው ተስፋ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “አባትህንና እናትህን አክብር፤” ከተስፋ ቃል ጋር የተሰጠ የመጀመሪያው ትእዛዝ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “አባትህንና እናትህን አክብር” የሚለው ትእዛዝ የተስፋ ቃል ያለበት የመጀመሪያ ትእዛዝ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2-3 መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት።

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 6:2
13 Referencias Cruzadas  

“አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድ​ርም ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም።


አባቱንና እናቱን የሚያማ ብርሃኑ ይጠፋል፥ የዐይኖቹ ብሌንም ጨለማን ያያል።


ኤር​ም​ያ​ስም ሬካ​ባ​ው​ያ​ንን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ባ​ታ​ች​ሁን የኢ​ዮ​ና​ዳ​ብን ትእ​ዛዝ ሰም​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ሁሉ ጠብ​ቃ​ች​ኋ​ልና፥ ያዘ​ዛ​ች​ሁ​ንም ሁሉ አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥


በም​ት​ኖ​ሩ​ባት ምድር ላይ ብዙ ዘመን እን​ድ​ት​ኖሩ፥ በዕ​ድ​ሜ​አ​ችሁ ሙሉ በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​መጡ እንጂ ቤትን አት​ሥሩ፤ ዘር​ንም አት​ዝሩ፤ ወይ​ንም አት​ት​ከሉ፤ አን​ዳ​ችም አይ​ሁ​ን​ላ​ችሁ።


በአ​ንቺ ውስጥ አባ​ት​ንና እና​ትን አቃ​ለሉ፤ በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ጻ​ተ​ኛው ላይ በደ​ልን አደ​ረጉ፤ በአ​ንቺ ውስጥ ድሀ አደ​ጉ​ንና መበ​ለ​ቲ​ቱን አስ​ጨ​ነቁ።


እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፣ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።


ለሁ​ሉም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው አድ​ርጉ፤ ግብር ለሚ​ገ​ባው ግብ​ርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚ​ገ​ባው ቀረ​ጥን ስጡ፤ ዐሥ​ራት ለሚ​ገ​ባው ዐሥ​ራ​ትን ስጡ፤ ሊፈ​ሩት የሚ​ገ​ባ​ውን ፍሩ፤ ክብር የሚ​ገ​ባ​ው​ንም አክ​ብሩ።


መል​ካም ይሆ​ን​ልህ ዘንድ፥ በም​ድር ላይም ዕድ​ሜህ ይረ​ዝም ዘንድ።”


“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ያ​ቃ​ልል ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ዘ​ዘህ አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም፥ መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ።


ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ፥ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos