Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤፌሶን 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሁለ​ቱን አንድ ያደ​ረገ ሰላ​ማ​ችን እርሱ ነውና፥ በሥ​ጋ​ውም በመ​ካ​ከል የነ​በ​ረ​ውን የጥል ግድ​ግዳ አፍ​ርሶ ጥልን ሻረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሁለቱን አንድ ያደረገ፣ የሚለያየውንም የጥል ግድግዳ ያፈረሰ ሰላማችን እርሱ ራሱ ነውና፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፥ ሁለቱን አንድ ያደረገ፥ እርሱ ሰላማችን ነውና፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ለያይቶን የነበረውን የጥል ግድግዳ ያፈረሰና አይሁድንና አሕዛብን አንድ ያደረገ ሰላማችን ክርስቶስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14-15 እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 2:14
28 Referencias Cruzadas  

በዚ​ህም አይ​ሁ​ዳዊ፥ ወይም አረ​ማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አንድ ናች​ሁና።


በእ​ርሱ ዘንድ አይ​ሁ​ዳዊ፥ ግሪ​ካ​ዊም፥ የተ​ገ​ዘረ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም፥ አረ​መ​ኔም፥ ባላ​ገ​ርም፥ ቤተ ሰብ​እና አሳ​ዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክር​ስ​ቶስ ለሁሉ በሁ​ሉም ዘንድ ነው።


በአ​ንድ አካል የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​ለት የክ​ር​ስ​ቶስ ሰላም በል​ባ​ችሁ ጸንቶ ይኑር፤ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በማ​መ​ስ​ገን ኑሩ።


ሁለ​ቱ​ንም አድሶ አንድ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ በሥ​ር​ዐቱ የት​እ​ዛ​ዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕር​ቅ​ንም አደ​ረገ።


ሁሉ​ንም በእ​ርሱ ይቅር ይለው ዘንድ በመ​ስ​ቀሉ ባፈ​ሰ​ሰው ደም በም​ድ​ርና በሰ​ማ​ያት ላሉ ሰላ​ምን አደ​ረገ።


ከዚህ ዓለም ኑሮ ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ታ​ችሁ እን​ደ​ገና በዓ​ለም እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች እን​ዴት ትሠ​ራ​ላ​ችሁ?


እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ከጸ​ደ​ቅን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰላ​ምን እና​ገ​ና​ለን።


ቃሉን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላከ፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምን ነገ​ራ​ቸው፤ እር​ሱም የሁሉ ገዢ ነው።


ጴጥ​ሮ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለአ​ይ​ሁ​ዳዊ ሰው ሄዶ ከባ​ዕድ ወገን ጋር መቀ​ላ​ቀል እን​ደ​ማ​ይ​ገ​ባው ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለእኔ ግን ከሰው ማን​ንም ቢሆን እን​ዳ​ል​ጸ​የ​ፍና ርኩስ ነው እን​ዳ​ልል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​የኝ።


በዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን ደም ለበ​ጎች ትልቅ እረኛ የሆ​ነ​ውን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው፥


“ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር።


ከዚህ ቦታ ያይ​ደሉ ሌሎች በጎ​ችም አሉኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ወደ​ዚህ አመ​ጣ​ቸው ዘንድ ይገ​ባ​ኛል፤ ቃሌ​ንም ይሰ​ሙ​ኛል፤ ለአ​ንድ እረ​ኛም አንድ መንጋ ይሆ​ናሉ።


በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ለነ​በ​ሩት ብር​ሃ​ኑን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ፥ እግ​ሮ​ቻ​ች​ን​ንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ።”


ይህም ለሰላም ይሆናል፥ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ምድራችንንም በረገጠ ጊዜ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።


አብ​ር​ሃ​ምም ከገ​ን​ዘቡ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ሰጠው፤ መጀ​መ​ሪያ የስሙ ትር​ጓሜ የጽ​ድቅ ንጉሥ ነበር፤ በኋ​ላም የሳ​ሌም ንጉሥ ተባለ፤ የሰ​ላም ንጉሥ ማለት ነው።


ከእ​ርሱ የተ​ነሣ አካል ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ክፍል በልክ እን​ደ​ሚ​ሠራ፥ በተ​ሰ​ጠው በሥር ሁሉ እየ​ተ​ጋ​ጠ​መና እየ​ተ​ያ​ያዘ፥ ራሱን በፍ​ቅር ለማ​ነጽ አካ​ሉን ያሳ​ድ​ጋል።


በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያሉ ነገ​ዶች ሁሉ ለሚ​ጠ​ሩት ለእ​ርሱ፤


በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”


ስለ ሕዝብ ብቻ አል​ነ​በ​ረም፤ የተ​በ​ተ​ኑ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ዘንድ ነው እንጂ።


እርሱ የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይሸከማል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይነግሣል፣ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፥ የሰላምም ምክር በሁለቱ መካከል ይሆናል።


መጥ​ቶም፤ ቀር​በን ለነ​በ​ር​ነው ሰላ​ምን፥ ርቃ​ችሁ ለነ​በ​ራ​ች​ሁት ለእ​ና​ን​ተም ሰላ​ምን ሰጠን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios