Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤፌሶን 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ስለ እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማመ​ስ​ገ​ን​ንና በጸ​ሎ​ቴም እና​ን​ተን ማሰ​ብን አላ​ቋ​ረ​ጥ​ሁም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በጸሎቴ እያስታወስኋችሁ ስለ እናንተ ምስጋና ማቅረብን አላቋረጥሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለ እናንተን በጸሎቴ ባስታወስኩ ቍጥር ምስጋናዬን አላቋረጥኩም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እናንተን በጸሎቴ እያስታወስኩ በእናንተ ምክንያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረቤን አላቋርጥም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ስለ እናንተ እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም፤

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 1:16
11 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚ​ህም እኛ ዜና​ች​ሁን ከሰ​ማን ጀምሮ፥ በፍ​ጹም ጥበ​ብና በፍ​ጹም መን​ፈ​ሳዊ ምክር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ ማወ​ቅን ትፈ​ጽሙ ዘንድ፥ ስለ እና​ንተ መጸ​ለ​ይ​ንና መለ​መ​ንን አል​ተ​ው​ንም።


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዘወ​ትር ስለ እና​ንተ እና​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለን።


ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤


በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ሥራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤


ደግሞ መል​ካ​ሙ​ንና ቅኑን መን​ገድ አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ስለ እና​ንተ መጸ​ለ​ይ​ንና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማገ​ል​ገ​ልን በመ​ተው እር​ሱን እበ​ድል ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን አያ​ድ​ር​ግ​ብኝ።


ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን በቅ​ጥ​ርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁ​ሜ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስቡ ከቶ ዝም አይ​ሉም፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ከመ​ጮኽ ዝም አት​በል። እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ነ​ናል” አሉት።


ነገር ግን በጎ ነገር በተ​ደ​ረ​ገ​ልህ ጊዜ እኔን ዐስ​በኝ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አድ​ር​ግ​ልኝ፤ ስለ እኔም ለፈ​ር​ዖን አሳ​ስ​በህ ከዚህ እስር ቤት አው​ጣኝ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios