Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 32:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፦ ትታ​መ​ኑ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩት አማ​ል​ክት የት አሉ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 እንዲህም ይላል፤ “መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፣ እነዚያ አማልክታቸው የት አሉ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 እርሱም ሕዝቡን እንዲህ ይላል፦ ‘ይታመኑባቸው የነበሩት አምባዎች፥ አማልክቶቻቸው የት ናቸው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እግዚአብሔርም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ ጠየቀ፦ ‘የሚተማመኑባቸው አማልክቶቻቸው የት አሉ? ከዚያም የተማመኑበት አለት አማልክቶቻቸውስ የት አሉ’ ይላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 እርሱም ይላል፦ አማልክቶቻቸው የት ናቸው? 2 ይታመኑባቸው የነበሩት አማልክት?

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 32:37
8 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠባ​ቂዬ ነው፤ በእ​ር​ሱም እታ​መ​ና​ለሁ፤ ጋሻ​ዬና የመ​ድ​ኀ​ኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መድ​ኀ​ኒቴ ሆይ፥ ከግ​ፈኛ ታድ​ነ​ኛ​ለህ።


ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባ​ትህ ነቢ​ያ​ትና ወደ እና​ትህ ነቢ​ያት ሂድ፥” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “አይ​ደ​ለም፤ በሞ​ዓብ እጅ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን ሦስት ነገ​ሥ​ታት ጠር​ቶ​አ​ልን?” አለው።


በዚ​ያች ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ፥ እነ​ርሱ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው በአ​መ​ነ​ዘ​ሩና በሠ​ዉ​ላ​ቸው ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጠ​ሩህ፥ ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​በላ፥


ዓለ​ትም ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች ድልም ይሆ​ናሉ የሸ​ሸም ይያ​ዛል። በጽ​ዮን ዘርእ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ ሄደው ወደ​ሚ​ያ​ጥ​ኑ​ላ​ቸው፥ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ከቶ ወደ​ማ​ያ​ድ​ኗ​ቸው አማ​ል​ክት ይጮ​ኻሉ።


ለአ​ንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸው አማ​ል​ክ​ትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማ​ል​ክ​ትህ እንደ ከተ​ሞ​ችህ ቍጥር እን​ዲሁ ናቸ​ውና ይነሡ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ ያድ​ኑህ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በመ​ን​ገ​ዶ​ችዋ ቍጥር ለጣ​ዖት ሠዉ።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በእ​ና​ን​ተና በዚ​ህች ሀገር አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም ብለው ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ የነ​በሩ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችሁ ወዴት አሉ?


ሄዳ​ችሁ ወደ መረ​ጣ​ች​ኋ​ቸው አማ​ል​ክት ጩኹ፤ እነ​ር​ሱም በመ​ከ​ራ​ችሁ ጊዜ ያድ​ኑ​አ​ችሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos