Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 32:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ንስር ጫጩ​ቶ​ቹን በክ​ን​ፎቹ በታች እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስብ፥ በጎ​ኑም እን​ደ​ሚ​ያ​ቅፍ፥ በክ​ን​ፎቹ አዘ​ላ​ቸው፤ በደ​ረ​ቱም ተሸ​ከ​ማ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ንስር ጐጆዋን በትና፣ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፣ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ፣ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ንስር ጎጆዋን ቆስቁሳ፥ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ይወስደዋል፥ በክንፎቹም ያዝለዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በጫጩቶችዋ ላይ እንደምታንዣብብ፥ ጎጆዋን እንደምትጠብቅ ንስር፥ እርሱን ለመያዝ ክንፎቹን ይዘረጋል፤ በክንፎቹም ጫፍ ይደግፈዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ 2 በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ 2 ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ 2 በክንፎቹም አዘላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 32:11
13 Referencias Cruzadas  

በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን፥ እንደ ንስር ክን​ፍም እንደ ተሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ወደ እኔም እን​ዳ​መ​ጣ​ኋ​ችሁ አይ​ታ​ች​ኋል።


እስከ ሽም​ግ​ልና ድረስ እኔ ነኝ፤ እስከ ሽበ​ትም ድረስ እኔ ነኝ፤ እኔ እታ​ገ​ሣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ሠር​ቻ​ለሁ፤ እኔም ይቅር እላ​ለሁ፤ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ።


በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛም አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​አ​ክም አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ራሱ ያድ​ና​ቸ​ዋል እንጂ። እርሱ ይወ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና፥ ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ል​ምና እርሱ ተቤ​ዣ​ቸው፤ ተቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ በዘ​መ​ና​ቸ​ውም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አከ​በ​ራ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉና የሚ​ታ​ገሡ ግን ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወ​ጣሉ፤ ይሮ​ጣሉ፤ አይ​ታ​ክ​ቱ​ምም፤ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ራ​ቡ​ምም።


ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።


ዓለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ተፈ​ጠረ፥ የሚ​ታ​የ​ውም ነገር ከማ​ይ​ታ​የው እንደ ሆነ በእ​ም​ነት እና​ው​ቃ​ለን።


እን​ደ​ሚ​በ​ርር ወፍ እን​ዲሁ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ይከ​ል​ላ​ታ​ልም፤ ይታ​ደ​ጋ​ታል፤ አል​ፎም ያድ​ና​ታል።


ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሓ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።


ምድር ግን ባዶ ነበ​ረች፤ አት​ታ​ይ​ምም ነበር፤ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ችም አል​ነ​በ​ረ​ችም፤ ጨለ​ማም በው​ኃው ላይ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በው​ኃው ላይ ይሰ​ፍፍ ነበር።


ስለ ብን​ያ​ምም እን​ዲህ አለ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ወ​ደደ በእ​ርሱ ዘንድ ተማ​ምኖ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዘ​መኑ ሁሉ ይጋ​ር​ደ​ዋል፤ በት​ከ​ሻ​ውም መካ​ከል ያድ​ራል።


ከወ​ር​ቅና ከክ​ቡር ዕንቍ ይልቅ ይወ​ደ​ዳል፤ ከማ​ርና ከማር ወለ​ላም ይልቅ ይጣ​ፍ​ጣል።


መታ​ጠ​ቂያ በሰው ወገብ ላይ እን​ደ​ም​ት​ጣ​በቅ፥ እን​ዲሁ ለስም፥ ለመ​መ​ኪ​ያና ለክ​ብር ሕዝብ ይሆ​ኑ​ልኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣ​ብ​ቄ​አ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙም።”


እኔም ኤፍ​ሬ​ምን ወደ​ድ​ሁት፤ በክ​ን​ዴም ተቀ​በ​ል​ሁት፤ እኔም እፈ​ው​ሳ​ቸው እንደ ነበ​ርሁ አላ​ወ​ቁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios