Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 26:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በዚ​ያም ወራት ወደ​ሚ​ሆ​ነው ካህን መጥ​ተህ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አስ​ታ​ው​ቃ​ለሁ’ በለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚያም ወቅት ለሚያገለግለው ካህን፣ “እግዚአብሔር ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እናገራለሁ” በለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚያም ወቅት ለሚያገለግለው ካህን፥ ‘ጌታ ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደገባሁ ዛሬ በጌታ እግዚአብሔር ፊት እናገራለሁ’ በለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚያን ወራት በሥልጣን ላይ ወዳለው ካህን ሄደህ እንዲህ በለው፦ ‘እኔ ዛሬ አስቀድሞ አምላክህ እግዚአብሔር ለእኛ ለልጆቻቸው እንዲሰጠን ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል ወደገባላቸው ምድር መግባቴን አረጋግጣለሁ።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በዚያም ወራት ወደሚሆነው ካህን መጥተህ፦ እግዚአብሔር ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አስታውቃለሁ በለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 26:3
13 Referencias Cruzadas  

በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”


በዚ​ህች ምድር ተቀ​መጥ፤ ከአ​ንተ ጋርም እሆ​ና​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለ​ሁም፤ ይህ​ችን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተም፥ ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለ​ሁና፥ ለአ​ባ​ት​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ል​ሁ​ለ​ትን መሐላ ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።


እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ግቡ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ርሱ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ይሰ​ጣት ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ውረሱ።


ሁለቱ ጠበ​ኞች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በካ​ህ​ና​ቱና በዚያ ዘመን በሚ​ፈ​ርዱ ፈራ​ጆች ፊት ይቆ​ማሉ፤


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከም​ት​ሰ​በ​ስ​በው ፍሬ ሁሉ ቀዳ​ም​ያት ውሰድ፤ በዕ​ን​ቅ​ብም አድ​ር​ገው፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።


ካህ​ኑም ዕን​ቅ​ቡን ከእ​ጅህ ወስዶ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ያኑ​ረው፤


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ታላቅ ካህን አለን።


በውኑ እን​ግ​ዲህ በስሙ እና​ምን ዘንድ የከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን ፍሬ የሚ​ሆን የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን በየ​ጊ​ዜው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልና​ቀ​ርብ አይ​ገ​ባ​ን​ምን?


ቅዱ​ስና ያለ ተን​ኰል፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም የተ​ለየ፥ ከሰ​ማ​ያ​ትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት ይገ​ባ​ናል።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos