Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የወ​ን​ድ​ምህ አህ​ያው ወይም በሬው በመ​ን​ገድ ወድቆ ብታይ ቸል አት​በ​ላ​ቸው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ጋር ሆነህ አነ​ሣ​ሣው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የወንድምህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታየው፣ በእግሩ እንዲቆምለት ርዳው እንጂ ዐልፈኸው አትሂድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የወንድምህ አህያ ወይም በሬው በመንገድ ወድቆ ብታይ ከእርሱ ጋር ሆነህ በማንሣት እርዳው እንጂ ቸል አትበለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “የእስራኤላዊ ወገንህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታይ ዝም ብለህ አትለፍ፤ ቆሞ እንዲሄድ እንስሳውን በማንሣት እርዳው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የወንድምህ አህያ ወይም በሬው በመንገድ ወድቆ ብታይ ከእርሱ ጋር ሆነህ አነሣሣው እንጂ ቸል አትበለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 22:4
10 Referencias Cruzadas  

ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።


እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወ​ጣ​ለሁ፤ ስለ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እጅግ ብወ​ዳ​ችሁ ራሴን ወደ​ድሁ።


የሚ​ገ​ባስ እና ብር​ቱ​ዎች ደካ​ሞ​ችን በድ​ካ​ማ​ቸው እን​ድ​ን​ረ​ዳ​ቸው ነው፤ ለራ​ሳ​ች​ንም አና​ድላ።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።


አህ​ያ​ውም ቢሆን፥ በሬ​ውም ቢሆን፥ ወይም ልብሱ ቢሆን እን​ዲሁ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ እን​ዲ​ሁም በወ​ን​ድ​ምህ በጠ​ፋ​በት ነገር ሁሉ ባገ​ኘ​ኸው ጊዜ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ቸል ልት​ለው አይ​ገ​ባ​ህም።


“ሴት የወ​ንድ ልብስ አት​ል​በስ፤ ወን​ድም የሴት ልብስ አይ​ል​በስ፤ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios