Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አሞጽ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እን​ድ​ት​ተው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብን ማን ያነ​ሣ​ዋል? ጥቂት ነውና” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚያም በኋላ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንድትተወው እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋመው ይችላል? ታናሽ ነው እኮ!” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እኔም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እንድትተው እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ታናሽ ነውና እንዴት ይቆማል?” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዚያን ጊዜ እኔ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ፦ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እባክህ እሳቱ እንዲቆም አድርግ! ሕዝብህ እስራኤል ዐቅም የሌላቸው ስለ ሆኑ እንዴት ተቋቊመው መኖር ይችላሉ?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንድትተው እለምንሃለሁ፥ ያዕቆብ ታናሽ ነውና እንዴት ይቆማል? አልሁ።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 7:5
9 Referencias Cruzadas  

የባ​ሪ​ያ​ህን ነፍስ ደስ አሰ​ኛት፥ ነፍ​ሴን ወደ አንተ አነ​ሣ​ለ​ሁና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች ካህ​ናት በወ​ለ​ሉና በም​ሥ​ዋዑ መካ​ከል እያ​ለ​ቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕ​ዝ​ብህ ራራ፤ አሕ​ዛ​ብም ይገ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ርስ​ት​ህን ለማ​ላ​ገጫ አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል፦ አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።


ከእ​ር​ሱም ዘንድ የም​ስ​ጋ​ናና የዘ​ፈን ድምፅ ይወ​ጣል፤ እኔም አበ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አያ​ን​ሱ​ምም።


ለጥ​ቂት ጊዜ ቍጣዬ ይበ​ር​ዳል፤ ነገር ግን መዓቴ በም​ክ​ራ​ቸው ላይ ይሆ​ናል።”


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘርን ባያ​ስ​ቀ​ር​ልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆ​ንን፥ እንደ ገሞ​ራም በመ​ሰ​ልን ነበር።


የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፣ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።


እነ​ዚ​ህን ሕዝብ ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይቅር እን​ዳ​ል​ሃ​ቸው፥ እንደ ምሕ​ረ​ትህ ብዛት የእ​ነ​ዚ​ህን ሕዝብ ኀጢ​አት ይቅር በል።”


ሲገ​ድ​ሉም እኔ ብቻ​ዬን ቀርቼ ሳለሁ በግ​ን​ባሬ ተደ​ፍቼ፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ወዮ! መዓ​ት​ህን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ስታ​ፈ​ስስ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ ሁሉ ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” ብዬ ጮኽሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios