Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዐሥራ ሁለ​ቱም ሐዋ​ር​ያት ሕዝ​ቡን ሁሉ ጠር​ተው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ትተን ማዕ​ድን እና​ገ​ለ​ግል ዘንድ የሚ​ገባ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ስለዚህ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ሌሎችን ደቀ መዛሙርት በአንድነት ሰብስበው እንዲህ አሉ፤ “እኛ የማእዱን አገልግሎት ለማስተናገድ ስንል የእግዚአብሔርን ቃል አገልግሎት መተው አይገባንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዐሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው “የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ስለዚህ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አማኞችን ሁሉ ሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “ምግብ ለማደል ብለን የእግዚአብሔርን ቃል የማስተማር ሥራችንን መተው አይገባንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው፦ “የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 6:2
10 Referencias Cruzadas  

እኔም እን​ዲህ ስል መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክ​ሁ​ባ​ቸው፥ “እኔ ታላቅ ሥራ እሠ​ራ​ለሁ፤ እወ​ር​ድም ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም። ስለ​ምን ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣ​ቴና በመ​ው​ረዴ ሥራው ይታ​ጐ​ላል? ሥራ​ውን እንደ ፈጸ​ምሁ እመ​ጣ​ለሁ።”


አሁ​ንሳ ምን ይሁን? ሕዝቡ ወደ​ዚህ እንደ መጣህ ይሰ​ሙና ይሰ​በ​ሰቡ ይሆ​ናል።


የበ​ደሉ ደብ​ዳቤ ሳይ​ኖር እስ​ረ​ኛን ወደ ንጉሥ መላክ አይ​ገ​ባ​ምና፤ ለእ​ኔም ነገ​ሩም ሆነ አስሮ መላኩ አስ​ቸ​ግ​ሮ​ኛል።”


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያይ​ደለ እና​ን​ተን ልን​ሰማ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይገ​ባ​ልን? እስኪ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


በዚ​ያም ወራት ደቀ መዛ​ሙ​ርት በበዙ ጊዜ ከግ​ሪክ የመጡ ደቀ መዛ​ሙ​ርት በአ​ይ​ሁድ ምእ​መ​ናን ላይ አን​ጐ​ራ​ጐ​ሩ​ባ​ቸው፤ የዕ​ለት የዕ​ለ​ቱን ምግብ ሲያ​ካ​ፍሉ ባል​ቴ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቸል ይሉ​ባ​ቸው ነበ​ርና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን በመ​ል​ካም የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላ​ቸ​ውን መን​ፈስ ቅዱ​ስና ጥበብ የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ለዚህ ሥራም እን​ሾ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።


የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos