Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ይዘ​ውት ወደ መቅ​ደስ ሲገቡ ሕዝቡ ሁሉ ደን​ግ​ጠው ወደ ሰሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ ወደ እነ​ርሱ ሮጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የተፈወሰውም ሰው ከጴጥሮስና ዮሐንስ ጋራ ጥብቅ ብሎ ዐብሯቸው ሳለ፣ ሕዝቡ ሁሉ በመገረም እነርሱ ወደ ነበሩበት “የሰሎሞን መመላለሻ” ወደተባለው ስፍራ እየሮጡ መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የዳነው ሰው ከጴጥሮስና ከዮሐንስ አልለይም በማለት ይዞአቸው ሳለ ሰዎቹ ተደንቀው “የሰሎሞን መመላለሻ” ወደሚባለው ስፍራ ወደ እነርሱ ሮጠው ሄዱ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 3:11
9 Referencias Cruzadas  

በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም፥ “ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆ​ናል፤ ይችም ከተማ ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ኖ​ር​ባ​ትም የለም ብለህ ስለ ምን ትን​ቢት ተና​ገ​ርህ?” ሕዝ​ቡም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ዮሐ​ን​ስን፥ “ሂዱና የም​ን​በ​ላ​ውን የፋ​ሲካ በግ አዘ​ጋ​ጁ​ልን” አላ​ቸው።


ያም አጋ​ን​ንት የወ​ጡ​ለት ሰው ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ዘንድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ማለ​ደው፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ በሰ​ሎ​ሞን ደጅ መመ​ላ​ለሻ ይመ​ላ​ለስ ነበር።


ይህ​ንም ቃል ሲና​ገሩ ሰም​ተው ሁሉም ደን​ግ​ጠው ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሁሉም በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ቋንቋ ሲና​ገሩ ሰም​ተ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የሚ​ሉ​ትን አጡ።


ጴጥ​ሮ​ስም ሕዝ​ቡን ባያ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ? እኛ​ንስ በኀ​ይ​ላ​ች​ንና በጽ​ድ​ቃ​ችን ይህን ሰው በእ​ግሩ እን​ዲ​ሄድ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ነው አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ለምን ታዩ​ና​ላ​ችሁ?


ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ዮሐ​ን​ስ​ንም ወደ መቅ​ደስ ሲገቡ አይቶ ምጽ​ዋት ይሰ​ጡት ዘንድ ለመ​ና​ቸው።


ጴጥ​ሮ​ስም ከዮ​ሐ​ንስ ጋር ትኩር ብሎ ተመ​ለ​ከ​ተው፥ “ወደ እኛ ተመ​ል​ከት” አለው፤


በሐ​ዋ​ር​ያት እጅም በሕ​ዝቡ ዘንድ ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ​ዎች ይሠሩ ነበር፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም በሰ​ሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ በአ​ን​ድ​ነት ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos