Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 28:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከሦ​ስት ወር በኋ​ላም በዚ​ያች ደሴት ወደ ከረ​መ​ችው ወደ እስ​ክ​ን​ድ​ርያ መር​ከብ ወጣን፤ በዚ​ያች መር​ከብ ላይም የዲ​ዮ​ስ​ቆ​ሮስ ምል​ክት ነበ​ረ​ባት፤ ይኸ​ውም “የመ​ር​ከ​በ​ኞች አም​ላክ” የሚ​ሉት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከሦስት ወር በኋላም፣ በደሴቲቱ ክረምቱን ቆሞ በሰነበተ በአንድ መርከብ ተነሥተን ጕዞ ጀመርን። ይህም መርከብ የእስክንድርያ ሲሆን፣ በላዩ ላይ የመንታ አማልክቱ የዲዮስቆሮስ አርማ ነበረበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከሦስት ወርም በኋላ በደሴቲቱ ከርሞ በነበረው በእስክንድርያው መርከብ ተነሣን፤ በእርሱም የዲዮስቆሮስ ዓላማ ነበረበት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሦስት ወር በማልታ ከቈየን በኋላ ክረምቱን በደሴቲቱ ባሳለፈው በእስክንድርያው መርከብ ተሳፍረን ተነሣን፤ መርከቡ ዲዮስቆሮስ የተባሉ የመንታ አማልክት አርማ ነበረበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከሦስት ወርም በኋላ በደሴቲቱ ከርሞ በነበረው በእስክንድርያው መርከብ ተነሣን፥ በእርሱም የዲዮስቆሮስ አላማ ነበረበት።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 28:11
9 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሆና​ችሁ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ፥ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተማ​ከሩ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን የም​ስ​ላ​ቸ​ውን እን​ጨት የሚ​ሸ​ከ​ሙና ያድን ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ችል አም​ላክ የሚ​ጸ​ልዩ ዕው​ቀት የላ​ቸ​ውም።


ሰዎ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ስእ​ለ​ት​ንም ተሳሉ።


መር​ከ​በ​ኞ​ቹም ፈሩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ አም​ላኩ ጮኸ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም እን​ድ​ት​ቀ​ል​ል​ላ​ቸው በው​ስ​ጥዋ የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መር​ከቡ ውስ​ጠ​ኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝ​ቶም ያን​ኳ​ርፍ ነበር።


በደ​ሴ​ቲ​ቱም ሁሉ ሲዘ​ዋ​ወሩ ጳፉ ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሱ፤ በዚ​ያም አንድ አይ​ሁ​ዳዊ የሆነ ሐሰ​ተኛ ነቢ​ይና አስ​ማ​ተኛ ሰው አገኙ፤ ስሙም በር​ያ​ሱስ ይባ​ላል።


በዚ​ያም የመቶ አለ​ቃው ወደ ኢጣ​ልያ የም​ት​ሄድ የእ​ስ​ክ​ን​ድ​ር​ያን መር​ከብ አገኘ፤ ወደ እር​ስ​ዋም አስ​ገ​ባን።


እጅግ ታላቅ ክብ​ርም አከ​በ​ሩን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ለመ​ሄድ በተ​ነ​ሣን ጊዜ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንን ስንቅ ሰጡን።


ከዚ​ያም ሄደን ወደ ሰራ​ኩስ ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ተቀ​መ​ጥን።


የነጻ ወጭ​ዎች ከም​ት​ባ​ለው ምኵ​ራ​ብም ከቀ​ሬ​ናና ከእ​ስ​ክ​ን​ድ​ርያ፥ ከቂ​ል​ቅ​ያና ከእ​ስያ የሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን ይከ​ራ​ከ​ሩት ነበር።


ለጣ​ዖ​ታት የተ​ሠ​ዋ​ውን ስለ​መ​ብ​ላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓ​ለም ከንቱ እን​ደ​ሆነ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ እና​ው​ቃ​ለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos