Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 24:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ፊል​ክስ ግን አይ​ሁድ ከጥ​ንት ጀምሮ የክ​ር​ስ​ቲ​ያ​ንን ወገ​ኖች ሕግና ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ቃ​ወሙ ያውቅ ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም “እን​ኪ​ያስ የሺ አለ​ቃው ሉስ​ዮስ በመጣ ጊዜ ነገ​ራ​ች​ሁን እና​ውቅ ዘንድ እን​መ​ረ​ም​ራ​ለን” ብሎ ቀጠ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ፊልክስ ግን የጌታን መንገድ በሚገባ ዐውቆ ስለ ነበር፣ “የጦር አዛዡ ሉስያስ ሲመጣ ለጕዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ ነገሩን በቀጠሮ አሳደረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና “የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ፤” ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ፊልክስ ግን ስለ ክርስትና እምነት በደንብ ያውቅ ስለ ነበር “የጦር አዛዡ ሉስዮስ በመጣ ጊዜ፥ ስለ ጉዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” ብሎ አሰናበታቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና፦ የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 24:22
11 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ።


እነ​ር​ሱም ብዙ ጊዜ እን​ዲ​ሰ​ነ​ብት ማለ​ዱት፤ ነገር ግን አል​ወ​ደ​ደም።


ዛሬም በደል ሳይ​ኖር በአ​መ​ጣ​ች​ሁ​ብን ክር​ክር እኛ እን​ቸ​ገ​ራ​ለ​ንና ስለ​ዚህ ክር​ክር የም​ን​ወ​ቃ​ቀ​ሰው ነገር የለም፥” ይህ​ንም ብሎ ሸን​ጎ​ውን ፈታ።


ሀገረ ገዢ​ውም እን​ዲ​ና​ገር ጳው​ሎ​ስን ጠቀ​ሰው፤ ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ አስ​ተ​ዳ​ዳሪ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንም ታው​ቃ​ለህ። አሁ​ንም ደስ እያ​ለኝ ክር​ክ​ሬን አቀ​ር​ባ​ለሁ።


ነገር ግን ይህን አረ​ጋ​ግ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ እኔ በሕግ ያለ​ውን፥ በነ​ቢ​ያ​ትም የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ አምኜ እነ​ርሱ ክህ​ደት ብለው በሚ​ጠ​ሩት ትም​ህ​ርት የአ​ባ​ቶ​ችን አም​ላክ አመ​ል​ከ​ዋ​ለሁ።


ከጥ​ቂት ቀንም በኋላ ፊል​ክስ ከአ​ይ​ሁ​ዳ​ዊት ሚስቱ ከድ​ሩ​ሲላ ጋር መጣ። ልኮም ጳው​ሎ​ስን አስ​ጠ​ራው፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስለ ማመ​ንም የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር ሰማው።


ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም ሊያ​ረ​ክስ ሲሞ​ክር ያዝ​ነው፤ እንደ ሕጋ​ች​ንም ልን​ፈ​ር​ድ​በት ፈል​ገን ነበር።


ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የም​ጽ​ፈው የታ​ወቀ ነገር የለ​ኝም። ስለ​ዚህ ከተ​መ​ረ​መረ በኋላ የም​ጽ​ፈ​ውን አገኝ ዘንድ ወደ እና​ንተ ይል​ቁ​ንም ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ ወደ አንተ አመ​ጣ​ሁት።


የአ​ይ​ሁ​ድን ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንና ክር​ክ​ራ​ቸ​ውን አጥ​ብ​ቀህ ታው​ቃ​ለ​ህና ታግ​ሠህ ታደ​ም​ጠኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ።


ምን​አ​ል​ባት በመ​ን​ገድ የሚ​ያ​ገ​ኘው ሰው ቢኖር ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እያ​ሰረ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ላሉት ምኵ​ራ​ቦች የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ ከሊቀ ካህ​ናቱ ለመነ።


ፈራ​ጆ​ቹም አጥ​ብ​ቀው ይመ​ረ​ም​ራሉ፤ ያም ምስ​ክር ሐሰ​ተኛ ምስ​ክር ሆኖ በወ​ን​ድሙ ላይ በሐ​ሰት ተና​ግሮ ቢገኝ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos