Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 21:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ወደ ሰፈ​ርም በደ​ረሰ ጊዜ ጳው​ሎስ ሻለ​ቃ​ውን፥ “ላነ​ጋ​ግ​ርህ ትፈ​ቅ​ድ​ል​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ሻለ​ቃ​ውም፥ “የጽ​ርዕ ቋንቋ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ወታደሮቹ ወደ ጦር ሰፈር ይዘውት ሊሄዱ ሲሉ፣ ጳውሎስ ጦር አዛዡን፣ “አንድ ነገር እንድነግርህ ፍቀድልኝ?” አለው። አዛዡም እንዲህ አለው፤ “የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ወደ ሰፈርም ሊያገቡት በቀረቡ ጊዜ፥ ጳውሎስ የሻለቃውን “አንድ ነገር ብነግርህ ትፈቅዳለህን?” አለው። እርሱም “የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ወታደሮች ወደ ጦር ሰፈራቸው ሊያስገቡት በቀረቡ ጊዜ ጳውሎስ የጦር አዛዡን “አንድ ነገር እንድነግርህ ትፈቅድልኛለህን?” አለው። አዛዡም “የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ወደ ሰፈርም ሊያገቡት በቀረቡ ጊዜ፥ ጳውሎስ የሻለቃውን፦ አንድ ነገር ብነግርህ ትፈቅዳለህን? አለው። እርሱም፦ የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህን?

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 21:37
8 Referencias Cruzadas  

በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነሡ ሊመ​ል​ሱ​ላ​ች​ሁና ሊከ​ራ​ከ​ሯ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ችሉ እኔ አፍ​ንና ጥበ​ብን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


ጳው​ሎ​ስም ወደ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሊገባ ወድዶ ነበር፤ ነገር ግን ደቀ መዛ​ሙ​ርት ከለ​ከ​ሉት።


ጳው​ሎ​ስም ሰላ​ምታ ካቀ​ረ​በ​ላ​ቸው በኋላ በእ​ርሱ ሐዋ​ር​ያ​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።


ሕዝ​ቡም እኩ​ሌ​ቶቹ እን​ዲህ ነው፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አይ​ደ​ለም እያሉ ይጮሁ ነበር፤ ሻለ​ቃ​ውም ሕዝቡ የሚ​ታ​ወ​ክ​በ​ትን ርግ​ጡን ማወቅ ተሣ​ነው፤ ወደ ወታ​ደ​ሮ​ቹም ሰፈር እን​ዲ​ወ​ስ​ዱት አዘዘ።


የሻ​ለ​ቃው የሚ​ጮ​ሁ​በት ስለ ምን እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር እን​ዲ​ያ​ገ​ቡ​ትና እየ​ገ​ረፉ የሠ​ራ​ውን እን​ዲ​መ​ረ​ም​ሩት አዘዘ።


እጅ​ግም በታ​ወኩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቁት የሻ​ለ​ቃው ፈራና መጥ​ተው ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አው​ጥ​ተው ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ወታ​ደ​ሮ​ቹን አዘዘ።


የጳ​ው​ሎ​ስም የእ​ኅቱ ልጅ ምክ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ሄዶ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ገባና ለጳ​ው​ሎስ ነገ​ረው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos