Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 21:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ሕዝ​ቡም እኩ​ሌ​ቶቹ እን​ዲህ ነው፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አይ​ደ​ለም እያሉ ይጮሁ ነበር፤ ሻለ​ቃ​ውም ሕዝቡ የሚ​ታ​ወ​ክ​በ​ትን ርግ​ጡን ማወቅ ተሣ​ነው፤ ወደ ወታ​ደ​ሮ​ቹም ሰፈር እን​ዲ​ወ​ስ​ዱት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ሕዝቡም ከፊሉ አንድ ነገር ሲናገር፣ ከፊሉ ደግሞ ሌላ ይናገር ነበር፤ ከጫጫታው የተነሣም አዛዡ ምንም ነገር ሊሰማ አልቻለም፤ ስለዚህ ጳውሎስ ወደ ጦር ሰፈር እንዲወሰድ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ሕዝቡም እኩሌቶቹ እንዲህ እኩሌቶቹም እንዲያ እያሉ ይጮኹ ነበር፤ ስለ ጫጫታውም እርግጡን ማወቅ ባልተቻለ ጊዜ፥ ወደ ወታደሮች ሰፈር ይወስዱት ዘንድ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ሕዝቡም አንዳንዶቹ አንድ ነገር ሲሉ፥ ሌሎች ሌላ ነገር ይሉ ነበር፤ አዛዡ ከሕዝቡ ጩኸት የተነሣ እርግጠኛውን ነገር ለማወቅ ስላልቻለ ጳውሎስን ወደ ወታደሮቹ ሰፈር እንዲወስዱት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ሕዝቡም እኵሌቶቹ እንዲህ እኵሌቶቹም እንዲያ እያሉ ይጮኹ ነበር፤ ስለ ጫጫታውም እርግጡን ማወቅ ባልተቻለ ጊዜ፥ ወደ ወታደሮች ሰፈር ይወስዱት ዘንድ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 21:34
8 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም በጨ​ዋ​ታው ቦታ የነ​በሩ ሰዎች እየ​ጮኹ ቈዩ፤ በሌ​ላም ቋንቋ የሚ​ጮሁ ነበሩ፤ በጉ​ባ​ኤው ታላቅ ድብ​ል​ቅ​ልቅ ሆኖ ነበ​ርና፤ ከእ​ነ​ርሱ የሚ​በ​ዙት ግን በምን ምክ​ን​ያት እንደ ተሰ​በ​ሰቡ አያ​ው​ቁም ነበር።


ወደ ሰፈ​ርም በደ​ረሰ ጊዜ ጳው​ሎስ ሻለ​ቃ​ውን፥ “ላነ​ጋ​ግ​ርህ ትፈ​ቅ​ድ​ል​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ሻለ​ቃ​ውም፥ “የጽ​ርዕ ቋንቋ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አለው።


የሻ​ለ​ቃው የሚ​ጮ​ሁ​በት ስለ ምን እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር እን​ዲ​ያ​ገ​ቡ​ትና እየ​ገ​ረፉ የሠ​ራ​ውን እን​ዲ​መ​ረ​ም​ሩት አዘዘ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም የሻ​ለ​ቃው አይ​ሁድ የሚ​ከ​ሱት ስለ ምን እን​ደ​ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ​ደና ከእ​ስ​ራቱ ፈታው፤ ሊቃነ ካህ​ና​ቱና ሸን​ጎ​ውም ሁሉ እን​ዲ​መጡ አዘዘ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አም​ጥቶ በፊ​ታ​ቸው አቆ​መው።


እጅ​ግም በታ​ወኩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቁት የሻ​ለ​ቃው ፈራና መጥ​ተው ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አው​ጥ​ተው ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ወታ​ደ​ሮ​ቹን አዘዘ።


የጳ​ው​ሎ​ስም የእ​ኅቱ ልጅ ምክ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ሄዶ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ገባና ለጳ​ው​ሎስ ነገ​ረው።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ይሄዱ ዘንድ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ትተው እነ​ርሱ ወደ ሰፈር ተመ​ለሱ።


ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የም​ጽ​ፈው የታ​ወቀ ነገር የለ​ኝም። ስለ​ዚህ ከተ​መ​ረ​መረ በኋላ የም​ጽ​ፈ​ውን አገኝ ዘንድ ወደ እና​ንተ ይል​ቁ​ንም ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ ወደ አንተ አመ​ጣ​ሁት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos