Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ነገር ግን የማ​ይ​ሆ​ነ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ የሙ​ሴ​ንም ሕግ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ዋ​ቸው፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያሉ ያመኑ አይ​ሁ​ድ​ንም ልጆ​ቻ​ቸ​ውን እን​ዳ​ይ​ገ​ርዙ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ እን​ዳ​ይ​ፈ​ጽሙ እን​ደ​ም​ት​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸው ስለ አንተ ነግ​ረ​ዋ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በአሕዛብ መካከል የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ ሙሴን እንዲተዉና ልጆቻቸውን እንዳይገርዙ፣ በቈየው ልማዳችን መሠረት እንዳይኖሩ እንደምታስተምር ስለ አንተ ተነግሯቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ በሥርዓትም እንዳይሄዱ ብለህ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁድ ሁሉ ሙሴን ይክዱ ዘንድ እንድታስተምር ስለ አንተ ነግረዋቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አንተ በአሕዛብ መካከል የሚኖሩትን አይሁድ ሁሉ ‘ልጆቻችሁን አትግረዙ ወይም ሥርዓቶችን አትፈጽሙ’ እያልክ በማስተማር የሙሴን ሕግ እንዲሽሩ ታደርጋለህ እየተባለ የሚወራውን ሰምተዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ በሥርዓትም እንዳይሄዱ ብለህ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁድ ሁሉ ሙሴን ይክዱ ዘንድ እንድታስተምር ስለ አንተ ነግረዋቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 21:21
12 Referencias Cruzadas  

ጳው​ሎ​ስም ከእ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ፤ በዚ​ያም ሀገር ስለ አሉት አይ​ሁድ ወስዶ ገረ​ዘው፤ አባቱ አረ​ማዊ እንደ ነበረ ሁሉም ያውቁ ነበ​ርና።


አሁ​ንሳ ምን ይሁን? ሕዝቡ ወደ​ዚህ እንደ መጣህ ይሰ​ሙና ይሰ​በ​ሰቡ ይሆ​ናል።


እየ​ጮ​ሁም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ ርዱን፤ በየ​ስ​ፍ​ራው ሕዝ​ባ​ች​ንን፥ ኦሪ​ት​ንም፥ ይህ​ንም ስፍራ የሚ​ቃ​ወም ትም​ህ​ርት ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እነሆ፥ ይህ ሰው ነው፤ አሁ​ንም አረ​ማ​ው​ያ​ንን ወደ መቅ​ደስ አስ​ገባ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም አረ​ከሰ።


ከሦ​ስት ቀንም በኋላ ጳው​ሎስ የአ​ይ​ሁ​ድን ታላ​ላቅ ሰዎች ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ቢሆን፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ ላይ ቢሆን ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር የለም፤ ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ታሰ​ርሁ ለሮም ሰዎች አሳ​ል​ፈው ሰጡኝ።


ሁልጊዜ ኀጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos