Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከእ​ነ​ር​ሱም ከተ​ለ​የን በኋላ እኛ በመ​ር​ከብ ተሳ​ፍ​ረን፥ መን​ገ​ዳ​ች​ን​ንም አቅ​ን​ተን ወደ ቆስ መጣን፤ በበ​ነ​ጋ​ውም ወደ ሮዶስ፥ ከዚ​ያም ወደ ጳጥራ ገባን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከእነርሱ ከተለየን በኋላ ቀጥታ በመርከብ ወደ ቆስ ተጓዝን፤ በማግስቱም ወደ ሩድ፣ ከዚያም ወደ ጳጥራ አመራን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከእነርሱም ተለይተን ተነሣን፤ በቀጥታም ሄደን ወደ ቆስ በነገውም ወደ ሩድ ከዚያም ወደ ጳጥራ መጣን፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከእነርሱ ከተለየን በኋላ በመርከብ ተሳፈርንና በቀጥታ ቆስ ወደምትባል ደሴት ሄድን፤ በማግስቱም ወደ ሩድ ደሴት ደረስን፤ ከዚያም ወደ ጳጥራ ከተማ ሄድን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከእነርሱም ተለይተን ተነሣን፤ በቀጥታም ሄደን ወደ ቆስ በነገውም ወደ ሩድ ከዚያም ወደ ጳጥራ መጣን፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 21:1
8 Referencias Cruzadas  

ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ከፈ​ጸመ በኋላ ስም​ዖ​ንን፥ “ወደ ጥልቁ ባሕር ፈቀቅ በል፤ መረ​ቦ​ቻ​ች​ሁ​ንም ለማ​ጥ​መድ ጣሉ” አለው።


ከዕ​ለ​ታት በአ​ን​ዲት ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ እርሱ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ ወጣና፥ “ኑ ወደ ባሕሩ ማዶ እን​ሻ​ገር” አላ​ቸው እነ​ር​ሱም ሄዱ።


በተ​ነ​ሣ​ንም ጊዜ ወደ እስያ በም​ት​ሄድ በአ​ድ​ራ​ማ​ጢስ መር​ከብ ተሳ​ፈ​ርን፤ የተ​ሰ​ሎ​ንቄ ሀገር ሰው የሚ​ሆን መቄ​ዶ​ን​ያ​ዊው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስም አብ​ሮን ሄደ።


ከዚ​ያም ወጥ​ተን ነፋስ ፊት ለፊት ነበ​ርና በቆ​ጵ​ሮስ በኩል ዐለ​ፍን።


እኛ ግን ወንድሞች ሆይ! በልብ ያይደለ ፊት ለፊት ለጥቂት ጊዜ አጥተናችሁ፥ በብዙ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት እጅግ ሞከርን፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos