Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እንደ እሳት የተ​ከ​ፋ​ፈሉ የእ​ሳት ላን​ቃ​ዎ​ችም ታዩ​አ​ቸው፤ በሁ​ሉም ላይ ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የእሳት ምላሶች የሚመስሉም ታዩአቸው፤ ተከፋፍለውም በእያንዳንዳቸው ላይ ዐረፉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የእሳት ነበልባሎች የሚመስሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ ተከፋፍለውም በእያንዳንዳቸው ላይ ዐረፉባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 2:3
18 Referencias Cruzadas  

እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤


በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድን​ጋ​ዩ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ቅቅ መዶሻ አይ​ደ​ለ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሁሉም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተሞሉ፤ ይና​ገሩ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እንደ አደ​ላ​ቸው መጠ​ንም እየ​ራ​ሳ​ቸው በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ይና​ገሩ ጀመሩ።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲህ አሉ፥ “በመ​ን​ገድ ሲነ​ግ​ረን፥ መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም ሲተ​ረ​ጕ​ም​ልን ልባ​ችን ይቃ​ጠ​ል​ብን አል​ነ​በ​ረ​ምን?”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እነሆ፥ እነ​ርሱ አንድ ወገን ናቸው፤ ለሁ​ሉም አንድ ቋንቋ አላ​ቸው፤ ይህ​ንም ለማ​ድ​ረግ ጀመሩ፤ አሁ​ንም ያሰ​ቡ​ትን ሁሉ መሥ​ራ​ትን አይ​ተ​ዉም።


በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤


ለአ​ን​ዱም ተአ​ም​ራ​ትን ማድ​ረግ፥ ለአ​ን​ዱም ትን​ቢ​ትን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም መና​ፍ​ስ​ትን መለ​የት፥ ለአ​ን​ዱም በልዩ ዓይ​ነት ልሳን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም በል​ሳ​ኖች የተ​ነ​ገ​ረ​ውን መተ​ር​ጐም ይሰ​ጠ​ዋል።


ከቀ​ር​ጤ​ስና ከዐ​ረ​ብም የመ​ጣን፥ እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጌት​ነት በየ​ሀ​ገ​ራ​ችን ቋንቋ ሲና​ገሩ እን​ሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።”


ኢየሱስም መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።


ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”


አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በሰውነታችን ክፍሎች መካከል ዐመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፤ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፤ በገሃነምም ይቃጠላል።


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


በጠ​ራ​ሁህ ጊዜ ጠላ​ቶች ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ፤ አንተ አም​ላኬ እንደ ሆንህ እነሆ፥ ዐወ​ቅሁ።


ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮስ ተነ​ሣና በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቆመ፤ መቶ ሃያ ያህል ሰዎ​ችም በዚያ ሳሉ እን​ዲህ አላ​ቸው።


ድን​ገ​ትም እንደ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ከሰ​ማይ ድምፅ መጣ፤ የነ​በ​ሩ​በ​ት​ንም ቤት ሞላው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios