Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 13:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩና አለ​ቆ​ቻ​ቸው ግን እር​ሱን አላ​ወ​ቁም፤ የነ​ቢ​ያት መጻ​ሕ​ፍ​ት​ንም በየ​ሰ​ን​በቱ ሁሉ ሲያ​ነቡ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ ነገር ግን ይሙት በቃ ፈረ​ዱ​በት፥ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ፈጸ​ሙ​በት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የኢየሩሳሌም ሰዎችና አለቆቻቸው ኢየሱስን አላወቁትም፤ ይሁን እንጂ በየሰንበቱ የሚነበበው የነቢያት ቃል እንዲፈጸም በርሱ ፈረዱበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን አላወቁም፤ በየሰንበቱም የሚነበቡትን የነቢያት መጻሕፍት ባለማስተዋላቸው በእርሱ ላይ በፈረዱበት ጊዜ ትንቢቱ ተፈጻሚ እንዲሆን አድርገዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 13:27
25 Referencias Cruzadas  

“አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ አለ​ቆ​ቻ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረጉ ይህን ባለ​ማ​ወቅ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት አው​ቃ​ለሁ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ እና ዐዋ​ቂ​ዎች ነን እን​ዳ​ትሉ ይህን ምሥ​ጢር ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፦ አሕ​ዛብ ሁሉ እስ​ኪ​ገቡ ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል እኩ​ሌ​ቶ​ችን የልብ ድን​ቍ​ርና አግ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


ሙሴም ከጥ​ንት ጀምሮ በየ​ከ​ተ​ማዉ የሚ​ሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ነበር፤ በየ​ም​ኵ​ራ​ቡም በየ​ሰ​ን​በቱ ያነ​ብ​ቡት ነበር።”


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና መኳ​ን​ን​ቶ​ቻ​ችን አሳ​ል​ፈው እንደ ሰጡት፥ ሞትም እንደ ፈረ​ዱ​በ​ትና እንደ ሰቀ​ሉት ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው የክ​ር​ስ​ቶስ የክ​ብሩ ወን​ጌል ብር​ሃን እን​ዳ​ያ​በ​ራ​ላ​ቸው የዚህ ዓለም አም​ላክ ልባ​ቸ​ውን አሳ​ው​ሮ​አ​ልና።


ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ልባ​ቸው ተሸ​ፍ​ኖ​አል፤ ያም መጋ​ረጃ ብሉይ ኪዳን በተ​ነ​በ​በት ዘመን ሁሉ ጸንቶ ኖሮ​አል፤ ክር​ስ​ቶስ እስ​ኪ​ያ​ሳ​ል​ፈው ድረስ አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ምና።


የዚህ ዓለም ሹሞ​ችም አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ይህ​ንስ ቢያ​ውቁ ኑሮ የክ​ብር ባለ​ቤ​ትን ባል​ሰ​ቀ​ሉ​ትም ነበር።


ከዚ​ህም በኋላ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጡ​በ​ትን ቀን ቀጠ​ሩ​ትና ብዙ​ዎች ወዳ​ረ​ፈ​በት ወደ እርሱ መጡ፤ ከጥ​ዋ​ትም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እየ​መ​ሰ​ከረ ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱ​ስም ከሙሴ ኦሪ​ትና ከነ​ቢ​ያት እየ​ጠ​ቀሰ ነገ​ራ​ቸው።


ነገር ግን ስለ ስሜ ይህን ሁሉ ያደ​ር​ጉ​ባ​ች​ኋል፤ የላ​ከ​ኝን አያ​ው​ቁ​ት​ምና።


አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፤


ይህ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ችሁ አብ​ንም፥ እኔ​ንም ስላ​ላ​ወቁ ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ውን ልጅ ከፍ ከፍ በአ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ አባቴ እንደ አስ​ተ​ማ​ረ​ኝም እን​ዲሁ እና​ገ​ራ​ለሁ እንጂ የም​ና​ገ​ረው ከእኔ አይ​ደ​ለም።


እርሱ ግን፥ “ጴጥ​ሮስ ሆይ፥ እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ እን​ደ​ማ​ታ​ው​ቀኝ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” አለው።


ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።


እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።


ጲላ​ጦ​ስም የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ች​ንና መኳ​ን​ን​ቱን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ጠራ​ቸው።


መጻ​ሕ​ፍ​ትን መር​ምሩ፤ በእ​ነ​ርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የም​ታ​ገኙ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልና፤ እነ​ር​ሱም የእኔ ምስ​ክ​ሮች ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios