Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አገረ ገዢ​ውም የሆ​ነ​ውን በአየ ጊዜ ተገ​ረመ፤ በጌ​ታ​ችን ትም​ህ​ር​ትም አመነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አገረ ገዥውም የሆነውን ነገር ባየ ጊዜ፣ በጌታ ትምህርት በመደነቅ አመነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚያን ጊዜ አገረ ገዢው የተደረገውን ባየ ጊዜ ከጌታ ትምህርት የተነሣ ተገርሞ አመነ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አገረ ገዢውም የሆነውን ነገር ባየ ጊዜ አመነ፤ ስለ ጌታ በሰማውም ትምህርት ተደነቀ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በዚያን ጊዜ አገረ ገዡ የተደረገውን ባየ ጊዜ ከጌታ ትምህርት የተነሣ ተገርሞ አመነ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 13:12
20 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም ብልህ ሰው በሆነ ሰር​ግ​ዮስ ጳው​ሎስ በሚ​ባል አገረ ገዢ ዘንድ ይኖር ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ሊሰማ ወድዶ በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን ወደ እርሱ ጠራ​ቸው።


ሁሉም የን​ግ​ግ​ሩን መከ​ና​ወን መሰ​ከ​ሩ​ለት፤ የአ​ን​ደ​በ​ቱ​ንም ቅል​ጥ​ፍና እያ​ደ​ነቁ፥ “ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይሉ ነበር።


በዚያ ቦታም አጠ​ገብ ስሙን ፑፕ​ል​ዮስ የሚ​ሉት የደ​ሴ​ቲቱ አለቃ መሬት ነበር፤ እር​ሱም ሦስት ቀን ሙሉ በደ​ስታ በቤቱ ተቀ​ብሎ አስ​ተ​ና​ገ​ደን።


ሰዎ​ቹም ሁሉ ዐሥራ ሁለት ያህሉ ነበር።


ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም በአ​ን​ጾ​ኪያ ቈዩ፤ ከሌ​ሎች ብዙ ሰዎች ጋርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰበኩ፤ አስ​ተ​ማ​ሩም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በሀ​ገሩ ሁሉ ተዳ​ረሰ።


ነገር ግን ይቃ​ወ​ሙት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ በጥ​በ​ብና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበ​ርና።


ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም መል​ሰው፥ “ያ ሰው እንደ ተና​ገ​ረው ያለ ከቶ ሰው አል​ተ​ና​ገ​ረም” አሉ​አ​ቸው።


ሁሉም ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነ​ሣ​ልን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና።”


የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።


እነ​ር​ሱም ከመ​ሰ​ከ​ሩና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ከተ​ና​ገሩ በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ በብ​ዙ​ዎች የሰ​ማ​ርያ መን​ደ​ሮ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አስ​ተ​ማሩ።


አስ​ማ​ተ​ኛው ኤል​ማ​ስም የስሙ ትር​ጓሜ እን​ዲህ ነበ​ረና፥ ገዥ​ውን ከማ​መን ሊከ​ለ​ክ​ለው ፈልጎ ተቃ​ወ​ማ​ቸው።


አሕ​ዛ​ብም ይህን ሰም​ተው ደስ አላ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አከ​በሩ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትም የተ​ዘ​ጋጁ ሁሉ አመኑ።


ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ጳው​ሎስ በር​ና​ባ​ስን፦“እን​ግ​ዲ​ህስ እን​መ​ለ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባስ​ተ​ማ​ር​ን​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ያሉ​ትን ወን​ድ​ሞች እን​ጐ​ብ​ኛ​ቸው፤ እን​ዴት እን​ዳ​ሉም እን​ወቅ” አለው።


ጋል​ዮ​ስም የአ​ካ​ይያ አገረ ገዢ በሆነ ጊዜ አይ​ሁድ ተባ​ብ​ረው በጳ​ው​ሎስ ላይ ተነሡ፤ ወደ ሸን​ጎም አመ​ጡት።


በእ​ስ​ያም ያሉ አይ​ሁ​ድና አረ​ማ​ው​ያን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እስ​ኪ​ሰሙ ድረስ እን​ደ​ዚሁ ሁለት ዓመት ኖረ።


እን​ዲ​ህም እያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በኀ​ይል ያድ​ግና ይበ​ረታ ነበር።


ድሜ​ጥ​ሮ​ስና ከእ​ርሱ ጋር ያሉ አን​ጥ​ረ​ኞች ግን በማ​ንም ላይ ጠብ እን​ዳ​ላ​ቸው እርስ በር​ሳ​ቸው ይከ​ራ​ከሩ፤ እነ​ሆም በከ​ተ​ማው ውስጥ ፍርድ ቤት አለ፤ ዳኞ​ችም አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios