Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 10:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ በግ​ልጥ እን​ዲ​ታ​ይም አደ​ረ​ገው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 እግዚአብሔር ግን በሦስተኛው ቀን ከሙታን አስነሣው፤ እንዲታይም አደረገው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 እርሱን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው፤ ይገለጥም ዘንድ ሰጠው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ነገር ግን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን ከሞት አስነሣውና እንዲገለጥ አደረገው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 እርሱን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው ይገለጥም ዘንድ ሰጠው፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 10:40
16 Referencias Cruzadas  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያስ​ነ​ሣው እርሱ እኛ​ንም እንደ እርሱ እን​ዲ​ያ​ስ​ነ​ሣን፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር በፊቱ እን​ዲ​ያ​ቆ​መን እና​ው​ቃ​ለን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን የሞ​ትን ማሰ​ሪያ ፈቶ ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ሞት እር​ሱን ሊይ​ዘው አይ​ች​ል​ምና።


በዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን ደም ለበ​ጎች ትልቅ እረኛ የሆ​ነ​ውን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው፥


ስለ​ዚህ ሕያ​ዋ​ን​ንና ሙታ​ንን ይገዛ ዘንድ ክር​ስ​ቶስ ሞተ፥ ተነ​ሣም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው እርሱ አድ​ሮ​ባ​ችሁ ባለ መን​ፈሱ ለሟች ሰው​ነ​ታ​ችሁ ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ታል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ በኀ​ይ​ሉና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ በመ​ነ​ሣቱ ስለ አሳየ ስለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥


በመ​ረ​ጠው ሰው እጅ በዓ​ለም በእ​ው​ነት የሚ​ፈ​ር​ድ​ባ​ትን ቀን ወስ​ኖ​አ​ልና፤ እር​ሱን ከሙ​ታን ለይቶ በማ​ስ​ነ​ሣ​ቱም ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት መል​ሶ​አ​ልና።”


የአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው ያይ​ደለ ይሁ​ዳም፥ “ጌታ ሆይ፥ ለዓ​ለም ያይ​ደለ ለእኛ ራስ​ህን ትገ​ልጥ ዘንድ እን​ዳ​ለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ምን​ድን ነው?” አለው።


እር​ሱን ኢየ​ሱ​ስን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ነ​ሣው፤ ለዚ​ህም እኛ ሁላ​ችን ምስ​ክ​ሮቹ ነን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios