Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 10:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ጴጥ​ሮ​ስም ወደ እነ​ዚያ ሰዎች ወረ​ደና፥ “እነሆ፥ የም​ት​ፈ​ል​ጉኝ እኔ ነኝ፤ ለምን መጥ​ታ​ች​ኋል?” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ጴጥሮስም ወርዶ፣ “እነሆ፤ የምትፈልጉት ሰው እኔ ነኝ፤ የመጣችሁበት ጕዳይ ምንድን ነው?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጴጥሮስም ወደ ሰዎቹ ወርዶ “እነሆ፥ የምትፈልጉኝ እኔ ነኝ፤ የመጣችሁበትስ ምክንያት ምንድነው?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ጴጥሮስም ወርዶ ወደ ሰዎቹ ሄደና “እነሆ፥ የምትፈልጉት ሰው እኔ ነኝ፤ የመጣችሁበት ምክንያት ምንድን ነው?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ጴጥሮስም ወደ ሰዎቹ ወርዶ፦ “እነሆ፥ የምትፈልጉኝ እኔ ነኝ፤ የመጣችሁበትስ ምክንያት ምንድር ነው?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 10:21
6 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም ስለ ላካ​ች​ሁ​ብኝ ሳል​ጠ​ራ​ጠር ወደ እና​ንተ መጣሁ፤ በምን ምክ​ን​ያት እንደ ጠራ​ች​ሁኝ እጠ​ይ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።”


ኢየሱስም መልሶ “ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?” አለው። ዕውሩም “መምህር ሆይ! አይ ዘንድ፤” አለው።


ተነ​ሥና ውረድ፤ ምንም ሳት​ጠ​ራ​ጠር ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሂድ፤ እኔ ልኬ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና።”


እነ​ር​ሱም፥ “የመቶ አለቃ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ጻድቅ ሰው ነው፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ወገ​ኖች ሁሉ የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ለት ነው፤ ቅዱስ መል​አክ ተገ​ልጦ አን​ተን ወደ ቤቱ እን​ዲ​ጠ​ራህ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ረ​ው​ንም እን​ዲ​ሰማ አዝ​ዞ​ታል፤” አሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios