Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 19:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከዚ​ህም በኋላ ንጉ​ሡን ሊቀ​በ​ለው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ፥ ከእኔ ጋር ስለ​ምን አል​ወ​ጣ​ህም?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እርሱም ንጉሡን ለመቀበል ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፣ “ሜምፊቦስቴ፣ ዐብረኸኝ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የሳኦል ልጅ መፊቦሼትም ንጉሡን ለመቀበል ወረደ። ንጉሡ ከተሰደደበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተመለሰበት ዕለት ድረስ ለእግሩ መጫሚያ አላደረገም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 መፊቦሼት ከኢየሩሳሌም ተነሥቶ ንጉሡን በሚቀበልበት ስፍራ በደረሰ ጊዜ ንጉሡ “መፊቦሼት ሆይ፥ ስለምን ከእኔ ጋር ሳትሄድ ቀረህ?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ንጉሡም ሊቀበለው ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦ ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ ከእኔ ጋር ስለ ምን አልወጣህም? አለው።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 19:25
3 Referencias Cruzadas  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኩሲን፥ “ስለ ወዳ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ቸር​ነት ይህ ነውን? ከወ​ዳ​ጅህ ጋር ያል​ሄ​ድህ ስለ ምን​ድን ነው?” አለው።


ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለዮ​ና​ታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበ​ረው። የሳ​ኦ​ልና የዮ​ና​ታን ወሬ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በመጣ ጊዜ የአ​ም​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግ​ዚ​ቱም አዝ​ላው ሸሸች፤ ልት​ሸ​ሽም ስት​ሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ነበረ።


የሳ​ኦ​ልም ልጅ የዮ​ና​ታን ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉሥ ዳዊ​ትም፥ “ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ አገ​ል​ጋ​ይህ” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos