Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 19:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በላ​ያ​ችን ላይ የቀ​ባ​ነው አቤ​ሴ​ሎ​ምም በጦ​ር​ነት ሞቶ​አል፤ አሁ​ንም ንጉ​ሡን ለመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዝም ትላ​ላ​ችሁ?” አሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቃል ወደ ንጉሥ ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በላያችን ሆኖ እንዲገዛን የቀባነው አቤሴሎም ደግሞ በጦርነት ሞቷል፤ ታዲያ ንጉሡን የመመለሱን ጕዳይ ለምንድን ነው ዝም የምትሉት?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በመላው የእስራኤል ነገዶችም፥ ሕዝቡ እንዲህ እያለ እርስ በርሱ ይከራከር ነበር፤ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ አውጥቶናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ የታደገን እርሱ ነው፤ አሁን ግን በአቤሴሎም ምክንያት ከአገር ሸሽቶ ሄዶአል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 መሪያችን ይሆን ዘንድ አቤሴሎምን ቀብተን አንግሠነው ነበር፤ ነገር ግን እርሱ በጦርነት ላይ ተገደለ፤ ታዲያ፥ ንጉሥ ዳዊትን መልሶ ለማምጣት የሚሞክር ሰው እንዴት ታጣ?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በላያችን እንዲሆን የቀባነው አቤሴሎም በሰልፍ ሞቶአል፥ አሁንም እንግዲህ ንጉሡን ለመመለስ ስለ ምን ዝም ትላላችሁ? እያለ እርስ በርሱ ይከራከር ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 19:10
9 Referencias Cruzadas  

ራሳ​ቸ​ውን አነ​ገሡ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አይ​ደ​ለም፤ አለ​ቆ​ች​ንም አደ​ረጉ፤ እኔም አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ ለጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ከብ​ራ​ቸ​ውና ከወ​ር​ቃ​ቸው ጣዖ​ታ​ትን ለራ​ሳ​ቸው አደ​ረጉ።


ኢዮ​አ​ብም፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር እን​ዲህ እዘ​ገይ ዘንድ አል​ች​ልም” ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ገና በዛፍ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከ​ላ​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “ምድ​ሪቱ እጅግ መል​ካም እንደ ሆነች አይ​ተ​ናል፤ ተነሡ፤ በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ውጣ፤ እና​ንተ ዝም ትላ​ላ​ች​ሁን? ትሄዱ ዘንድ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ለመ​ው​ረስ ትገቡ ዘንድ ቸል አት​በሉ።


ከመ​ላው ነገደ እስ​ራ​ኤል የተ​ሰ​በ​ሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ታድ​ጎ​ናል፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ኖ​ናል፤ አሁ​ንም ስለ አቤ​ሴ​ሎም ከሀ​ገ​ሩና ከመ​ን​ግ​ሥቱ ሸሸ።


ንጉሡ ዳዊ​ትም ለካ​ህ​ናቱ ለሳ​ዶ​ቅና ለአ​ብ​ያ​ታር ልኮ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለይ​ሁዳ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲህ ብላ​ችሁ ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደር​ሶ​አ​ልና ንጉ​ሡን ወደ ቤቱ ከመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዘገ​ያ​ችሁ?


ንጉ​ሡም ወደ ጌል​ገላ ተሻ​ገረ፤ ከመ​ዓ​ምም ከእ​ርሱ ጋር ተሻ​ገረ፤ የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ፥ ደግ​ሞም የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ እኩ​ሌታ ከን​ጉሡ ጋር ተሻ​ገሩ።


ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እን​ሽሽ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎም እጅ የም​ን​ድ​ን​በት የለ​ን​ምና፤ ፈጥኖ እን​ዳ​ይ​ዘን፥ ክፉም እን​ዳ​ያ​መ​ጣ​ብን፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በሰ​ልፍ ስለት እን​ዳ​ይ​መታ ፈጥ​ና​ችሁ እን​ሂድ” አላ​ቸው።


ንጉ​ሡና ከእ​ር​ሱም በኋላ ቤተ ሰቡ ሁሉ በእ​ግ​ራ​ቸው ወጡ፤ ንጉ​ሡም ቁባ​ቶቹ የነ​በሩ ዐሥ​ሩን ሴቶች ቤቱን ይጠ​ብቁ ዘንድ ተወ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios