Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሶር​ያ​ው​ያን በዚያ ተደ​ብ​ቀ​ዋ​ልና በዚያ ስፍራ እን​ዳ​ታ​ልፍ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ላከ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የእግዚአብሔርም ሰው፣ “ሶርያውያን በዚያ ታች ወርደዋልና በዚያ በኩል እንዳታልፍ ተጠንቀቅ” ሲል ለእስራኤል ንጉሥ ላከበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኤልሳዕ ግን “ሶርያውያን ደፈጣ አድርገው ስለሚጠብቁህ ወደዚያ ስፍራ አትቅረብ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኤልሳዕ ግን “ሶርያውያን ደፈጣ አድርገው ስለሚጠብቁህ ወደዚያ ስፍራ አትቅረብ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የእግዚአብሔርም ሰው “ሶርያውያን በዚያ ተደብቀዋልና በዚያ ስፍራ እንዳታልፍ ተጠንቀቅ፤” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 6:9
15 Referencias Cruzadas  

ሁለ​ቱም የዐ​መፅ ልጆች የሆኑ ሰዎች ገብ​ተው በፊቱ ቆሙ፤ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሡን ሰድ​በ​ሃል” ብለው መሰ​ከ​ሩ​በት። የዚያ ጊዜም ከከ​ተማ አው​ጥ​ተው በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ገደ​ሉት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ስለ አክዓብ ወደ ባሪ​ያው ወደ ኤል​ያስ መጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፦


ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች የአ​ንዱ ሚስት የሆ​ነች አን​ዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪ​ያህ ሞቶ​አል፤ ባሪ​ያ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆ​ቼን ባሪ​ያ​ዎች አድ​ርጎ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው መጥ​ቶ​አል” ብላ ወደ ኤል​ሳዕ ጮኸች።


ወደ ተራ​ራ​ውም ወደ ኤል​ሳዕ ደርሳ እግ​ሮ​ቹን ጨበ​ጠች፤ ግያ​ዝም ሊያ​ር​ቃት መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ነፍ​ስዋ አዝ​ና​ለ​ችና ተዋት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ከእኔ ሰው​ሮ​ታል፤ አል​ነ​ገ​ረ​ኝ​ምም” አለ።


መጥ​ታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ነገ​ረ​ችው፤ እር​ሱም፥ “ሄደሽ ዘይ​ቱን ሽጭ ዕዳ​ሽ​ንም ክፈዪ፤ በተ​ረ​ፈ​ውም ዘይት የአ​ን​ቺ​ንና የል​ጆ​ች​ሽን ሰው​ነት አድኚ” አላት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኤል​ሳዕ ወደ ነገ​ረው ስፍራ ላከ፤ አንድ ጊዜም ሳይ​ሆን፥ ሁለት ጊዜም ሳይ​ሆን በዚያ ራሱን አዳነ።


ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ነቢዩ ኤል​ሳዕ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በእ​ል​ፍ​ኝህ ውስጥ ሆነህ የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና ቃል​ህን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እርሱ ይነ​ግ​ረ​ዋል፤” አለ።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይዋጋ ነበር፤ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ጋር ተማ​ክሮ፥ “በዚህ ስውር ቦታ ተደ​ብ​ቀን እና​ድ​ራ​ለን።” አላ​ቸው።


የተ​ን​ኰ​ለ​ኞ​ችን ምክር ይለ​ው​ጣል፥ እጆ​ቻ​ቸ​ውም ቅን አይ​ሠ​ሩም።


ባለ​ጠ​ጎች ደኸዩ፥ ተራ​ቡም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ል​ጉት ግን ከመ​ል​ካም ነገር ሁሉ አል​ተ​ቸ​ገ​ሩም።


የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ ኃጥእ ግን የጥበብን ቃል ይንቃል።


ጌታ ሆይ! አስ​ታ​ው​ቀኝ፤ እኔም አው​ቃ​ለሁ፤ ያን​ጊ​ዜም ሥራ​ቸ​ውን ገለ​ጥ​ህ​ልኝ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።


ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፤ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos