Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ኤል​ሳ​ዕም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ያፈ​ርሁ ባል​ሆን ኖሮ አን​ተን ባል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ሁና ባላ​የሁ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኤልሳዕም እንዲህ አለው፤ “የማገለግለው የሰራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔርን፣ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባላከብር ኖሮ፣ አንተን አላይም ወይም ጕዳዬ አልልህም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ኤልሳዕም “እኔ በማገለግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! አንተን ለመርዳት ለመጣው ለይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ክብር ስል ነው እንጂ፥ ለአንተስ ምንም ነገር ላደርግልህ ባልተገባ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ኤልሳዕም “እኔ በማገለግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! አንተን ለመርዳት ለመጣው ለይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ክብር ስል ነው እንጂ፥ ለአንተስ ምንም ነገር ላደርግልህ ባልተገባ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ኤልሳዕም “በፊቱ የቆምሁት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔርን! የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ያላፈርሁ ብሆን ኖሮ አንተን ባልተመለከትሁና ባላየሁ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 3:14
12 Referencias Cruzadas  

በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።


ኤል​ያ​ስም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ ዛሬ ለእ​ርሱ እገ​ለ​ጣ​ለሁ” አለው።


ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ በፊቱ የነ​በ​ረ​ውን ሰው ገደለ፤ ደጋ​ግ​መ​ውም ገደሉ። ከዚ​ህም በኋላ ሶር​ያ​ው​ያን ሸሹ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴ​ርም በፈ​ጣን ፈረስ አመ​ለጠ።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አል​ቀ​በ​ልም” አለ። ይቀ​በ​ለ​ውም ዘንድ ግድ አለው፤ እርሱ ግን እንቢ አለ።


ደዌ​ያ​ቸው በዛ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተፋ​ጠኑ፤ በደም ማኅ​በ​ራ​ቸው አል​ተ​ባ​በ​ርም። ስማ​ቸ​ው​ንም በአፌ አል​ጠ​ራም።


እነሆ በም​ድ​ሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በአ​ለ​ቆ​ች​ዋና በካ​ህ​ናቷ ላይ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመ​ሸ​ገች ከተማ፥ እንደ ብረ​ትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።


ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos