Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ለግ​ብፅ ንጉሥ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ወስዶ ነበ​ርና የግ​ብፅ ንጉሥ ከዚያ ወዲህ ከሀ​ገሩ አል​ወ​ጣም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የባቢሎንም ንጉሥ ከግብጽ ደረቅ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ የነበረውን ግዛቱን ሁሉ ወስዶበት ስለ ነበር፣ የግብጽ ንጉሥ ከአገሩ ዳግም ለዘመቻ አልወጣም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የባቢሎን ንጉሥ ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ግብጽ ሰሜናዊ ጠረፍ ድረስ የግብጽ ይዞታ የነበረውን ሁሉ በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ ስለ ነበረ የግብጽ ንጉሥና ሠራዊቱ ከዚያን በኋላ ከግብጽ ውጪ ዘመቻ አላደረጉም፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የባቢሎን ንጉሥ ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ግብጽ ሰሜናዊ ጠረፍ ድረስ የግብጽ ይዞታ የነበረውን ሁሉ በቊጥጥሩ ሥር አድርጎ ስለ ነበረ የግብጽ ንጉሥና ሠራዊቱ ከዚያን በኋላ ከግብጽ ውጪ ዘመቻ አላደረጉም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የባቢሎንም ንጉሥ ለግብጽ ንጉሥ የነበረውን ሁሉ ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ወስዶ ነበርና የግብጽ ንጉሥ ከዚያ ወዲያ ከአገሩ አልወጣም።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 24:7
10 Referencias Cruzadas  

በግ​ብፅ ላይ፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ በከ​ር​ኬ​ማስ በነ​በ​ረው፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በመ​ታው በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ኒካዑ ሠራ​ዊት፥


በዚ​ያ​ችም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤


ዳር​ቻ​ውም ከአ​ሴ​ሞና ወደ ግብፅ ወንዝ ይዞ​ራል፤ ወሰኑ ባሕሩ ይሆ​ናል።


በዚያ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥ​ራል፤ እና​ን​ተም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአ​ንድ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ላ​ችሁ።


ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ግብፅ ምድር ዳርቻ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ድረስ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብ​ርም ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ሙሉ ለሰ​ሎ​ሞን ይገዙ ነበር።


ወደ አጽ​ሞ​ንም ያል​ፋል፤ በግ​ብ​ፅም ሸለቆ በኩል ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ፤ በደ​ቡብ በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው ይህ ነው።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ላይ ነኝ የጸ​ና​ች​ው​ንና የተ​ሰ​በ​ረ​ች​ው​ንም ክን​ዱን እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ሰይ​ፉ​ንም ከእጁ አስ​ጥ​ለ​ዋ​ለሁ።


ፈጣ​ኑም አያ​መ​ል​ጥም፤ ኀያ​ሉም አይ​ድ​ንም፤ በሰ​ሜን በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ በኩል ደክ​መው ወደቁ።


“የሰው ልጅ ሆይ! የግ​ብ​ፅን ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ንን ክንድ ሰብ​ሬ​አ​ለሁ፥ እነ​ሆም ይድን ዘንድ መድ​ኃ​ኒት ቀብ​ተው አያ​ደ​ር​ቁ​ትም፤ ሰይ​ፉ​ንም ለመ​ያዝ ኀይ​ልን ያገኝ ዘንድ አል​ታ​ሰ​ረም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios