Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ ከደ​መ​ናው የተ​ነሣ መቆ​ምና ማገ​ል​ገል አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የእግዚአብሔር ክብር የአምላክን ቤተ መቅደስ ሞልቶት ስለ ነበር፣ ከደመናው የተነሣ ካህናቱ አገልግሎታቸውን ማከናወን አልቻሉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የጌታም ክብር የጌታን ቤት ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ከደመናው የተነሣ መቆምና ማገልገል አልቻሉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእግዚአብሔርም ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ከደመናው የተነሣ መቆምና ማገልገል አልተቻላቸውም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 5:14
10 Referencias Cruzadas  

ደመ​ና​ውም በላዩ ስለ​ነ​በር ድን​ኳ​ኑም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ስለ ተሞላ ሙሴ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይገባ ዘንድ አል​ቻ​ለም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ቤቱን ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ ከደ​መ​ናው የተ​ነሣ ለማ​ገ​ል​ገል ይቆሙ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ በዚ​ያች ዕለት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ባት አል​ቻ​ሉም።


ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኀይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርም ከኪ​ሩ​ቤል ወጥቶ በቤቱ መድ​ረክ ላይ ቆመ፤ ቤቱም በደ​መ​ናው ተሞላ፤ አደ​ባ​ባ​ዩም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ፀዳል ተሞላ።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።


በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አዝ​ዛ​ለሁ፤ በክ​ብ​ሬም እቀ​ደ​ሳ​ለሁ።


ሰሎ​ሞ​ንም ይህን ጸሎት በፈ​ጸመ ጊዜ እሳት ከሰ​ማይ ወርዶ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ቱን ሁሉ በላ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ቤቱን ሞላ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ሆይ፥ በሰ​ማይ ያለህ አም​ላክ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንስ መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የም​ት​ገዛ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? ኀይ​ልና ችሎታ በእ​ጅህ ነው፤ ሊቋ​ቋ​ም​ህም የሚ​ችል የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios